የኤሬቻን ምስጋና በኣል አስመልክቶ ከሲዳማ ኤጄቶች የተላለፈ የመልካም ምኞት መልእክት

የስርወ ገዳ ባህላዊ የሽግግር ሙዳይ ከሆኑት ትሩፋቶች አንዱ ኢሬቻ ነው። የኢሬቻ በኣል የኦሮሞ ብቻ ሳይሆን የኛ የሲዳማዎች ጭምር ነው። በኣሉ ከኛ ከኩሻውያን የተበረከተ ለመላው አለም የሚተርፍ የሰላምና የብርሃን ጮራ ነው።

በነዚህ የብርሃን ወራቶች ጽልመቶች ይገፈፋሉ ጥላቻና ሸፍጦች ይንበረከካሉ። በጭጋጋማውና ጥቁር ሰማይ የተከደነው የተፈጥሮ እውነት ያለ ከልካይ የሚገለጥበት ግዜ ነው። ኢሬቻ የዚህ ተፈጥሯዊ ኩነት ማሳያ ተምሳሌት ናት።

በዚህ በኣል ፈጣሪ ይመሰገናል፡ ፈጣሪ ደግሞ እውነት ነው።
እኛ ሲዳማዎችም ይህን ኡደት ሆላ ሃላሌሆ እንላለን። እውነት ታሸንፋለች። ብትቀጥን እንጂ አትበጠስም። የዘንድሮ በኣል የዚህ ማሳያ ነው።

የዚህን አመት አከባበር ከሌሎቹ ግዚያት ለየት የሚያደርገው የኦሮሞ ህዝብ ለሌሎች ጭቁን ህዝቦች ጭምር የተረፈ ደማቅ የትግል ምእራፍ ላይ በደረሰበት ማግስት መሆኑ ነው። ለዘመናት ተዘግቶ የከረመው የፍንፍኔ ሃርሰዲ ከዘመናት በኋላ ደግም ክፍት መደረጉ ለዚህ ድል፡ትልቅ ማሳያ ነው።

የኦሮሞ እና የሲዳማ ህዝቦች ለብዙ ዘመናት እውነት ተከደኖባቸው በባህላቸው እንዳይኮሩ በሃብታቸው እንዳይወስኑ ሲደረጉ የኖሩ ህዝቦች ናቸው። የዚህ ታሪክ ምእራፍ ግን ላይመለስ ሊከደን ግዜው የተቃረበ ይመስላል። አስቸጋሪው ክረምት አልፎ ደማቁ የኢረቻ ወር መጥቷል። ሀምሌ እና ነሃሴ ምንም ያህል ጽልመታሞች ቢሆኑ እንኳ መስከረምንና ህዳርን የመቋቋም አቅም አይኖራቸውም።

እኛ ሲዳማዎች ባለፉት ወራቶች በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ከ100 በላይ ኤጄቶች ተገድለውብን የተቀሩት በእስር እንዲማቅቁ ተደርጎ ሌሎች በስደት እንዲንከራተቱ ሆኖ የክረምቱን ወራት አሳልፈናል። ይህም ሆኖ የመራራ ትግል ተምሳሌቶቻችን ከሆናችሁን ቄሮዎች ተምረን በብዙ ጽናትና ተስፋ ዛሬ ለኢሬቻ ወደ አደባባያችን ወጥተናል። ገድሎ ብቻ ሳይሆን ሞቶ ማሸነፍም እንደሚቻል የሰላምዊ አብዮት ጓዶቻችን(ቄሮች) አስተምረውናል። በዚህ መነሻ ዛሬ በሲዳማ መዲና በደማቅ ሁኔታ በሃዋሳ አክብረናል። በኣሉን ስናከብር ለአዲስ ትግልና መስዋእትነት ራሳችንን በማዘጋጀት ነው።

የቄሮና ኤጄቶ ትግል የእኔ ልብለጥ ትግል ሳይሆን የእኩልነት ትግል ነው። ይህንን እውነት ምድር የምትቀበልበት ግዜ እሩቅ አይደለም። እንደ አውሬ ስለው እና አስለው የጨፈጨፉን ጸረ ህብረ ብሄራዊነት ሀይሎች የእውነት ጸሀይ ስትወጣ ማፈራቸው አይቀርም። ውድ ኦሮሞ ወንድሞቻችን ቀጣዩ የምስጋና አመት ሌላ አዲስ ታሪክ ጽፋችሁ በአዲስ የትግል ምእራፍ የምትገለጡበት አመት እንዲሆን ምኞታችን ነው!!
ኤጄቶ
ሐዋሳ

ሲዱማ

ኢትዮጵያ

 

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከሲዳማ ኤጄቶ የተሰጠ መግለጫ

ላለፉት ሀያ ስምንት ዓመታት በአገራችን ሕዝቡን ያስከፋው የተበለሸ አሰራር እንዲቀር ወጣቱ የከፈለውና እየከፈለ የሚገኘው መስዋዕትነት ከፍተኛ ነው። በአገራችን የታየው የተስፋ ጭላንጭልም ደብዛው እንዳይጠፋ ከፍተኛ የሆነ የሞት የሽረት ትግል እያካሄደ ይገኛል። የሲዳማ ወጣትም በተካሄደው እና እየተካሄደ ባለው ትግል ከፍተኛ ተሳትፎ በማድረግ ኢ-ፍትሀዊ አሰራር፣ ሙስና፣ አድሏዊ አሰራር፣ ማንነት ማጥፋት እና ኢ-ሰብአዊ የሆኑ መንግስታዊ በደሎች ከህዝባችን ጫንቃ ላይ እንዲወገድ የበኩሉን ተወጥቷል፤ እየተወጣም ይገኛል። በተለይም የሲዳማ ሕዝብ ራሱን በራሱ ለማስተዳደር ለዘመናት ሲጠይቀው የነበረው ሕዝባዊ ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ቀዳሚውን የመሪነት ሚና ሲጫወት ቆይቷል።

ይህ የሕዝቦች የመብት ጥያቄ በህገ መንግስቱ መሰረት ምላሽ እንዲያገኝ የቀደሙቱ የሲዳማ ጀግኖች የማዕረግ ስያሜ ኤጄቶን መጠርያው በማድረግ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል በማቀፍ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቷል። ይሁን እንጂ የአገራችን ሕዝቦች እንደታዘባችሁት የኢትዮጵያ መንግስት ወቅቱን የጠበቀ ህገመንግስታዊ ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ ሳይሆን ቆይቷል። በተጨማሪም የብሄር ብሄረሰቦች ማንነት እኩልነት የማይፈልጉ እና ከታሪክ የማይማሩ ጥቂት ኃይሎች ብዙ መስዋዕት የተከፈለበትን ትግል ለመቀልበስ ክፍተኛ በጀት በመመደብ  በሚቆጣጠሯቸው ሚዲያወች ጭምር በመታገዝ የተቻላቸውን ፀረ-ሕዝባዊ እንቅስቃሴወችን አድርገዋል። ይሄው እኩያ ተግባራቸው በተደጋጋሚ በወጣቱ የነቃ ተሳትፎ እየከሸፈ ቢቆምም በመጨረሻ ከመንግስት ኢ-ህገመንግስታዊ አካሄድ ጋር ተደምሮ መንግስት ላይ ከፍተኛ ጫና በማሳረፍ መንግስት በሚያስተዳድረው ህዝብ ላይ ኢ-ሰብአዊ ጥቃት እንዲፈጽም አድርገዋል።

በሲዳማ ሕዝብ ጥያቄ ዙርያ በምርጫ ቦርድ የተሰጠውን  አወዛጋቢ መግለጫ እና ህዝበ ውሳኔ ለማካሄድ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ 11/11/11 ዓ. ም ማለቁን ተከትሎ በቀጣይ ጉዞ ላይ ለመመካከር በሕዝባዊ መገናኛ ስፍራ ጉዱማሌ ለመገናኘት በማቅናት ላይ የሚገኝ ህዝብ ላይ በተወሰደ ወታደራዊ እርምጃ በርካቶች ለሞትና ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በመላው ሲዳማ ዞን በተፈጠረ አለመረጋጋት የበርካታ ወገኖቻችን ንብረት ወድሟል፣በርካቶችም ተፈናቅለዋል። የመንግስት ወታደሮች በሕዝባችን ላይ የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ በየአካባቢው የተፈጠረው አለመረጋጋት ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንዳያመራ ሕዝብን ለማረጋጋት፣ አስከሬኖቹን በማንሳት ከተጎጂ ቤተሰቦች ጋር ጊዜ በማጥፋት እና የከፋ የንብረት ውድመት እንዳይከሰት ተጨማሪ ሰው እንዳይፈናቀል  እና የተፈናቀሉት ወደየ አካባቢያቸው ተመልሰው ኑሮአቸውን እንዲመሩ ኤጄቶ ከህብረተሰቡ ጋር በመመካከር ላይ የቆዬ ሲሆን በተከሰቱ ጉዳዮች ዙርያ የሚከተለውን ባለ ሰባት ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

1ኛ. የሕዝቡን ዴሞክራሲያዊ የመብት ጥያቄ ሀላፊነት በተሞላበት ሁኔታ መንግስት ከሕዝቡ ጋር በውይይት መፍታት እየቻለ፣ ለሰላማዊ ትግል ቦታ ባለመስጠት የብሄሩ የራስ የማስተዳደር ፍላጎት በኃይል እንዲጨፈለቅ ከሚፈልጉ ኃይላት ምክር በመቀበል የወሰደውን አረመኔያዊ የጭካኔ እርምጃ በጽኑ እናወግዛለን። በወታደራዊ ጥቃት ውድ ህይወታቸውን ላጡና ለአካል ጉዳት ለተዳረጉ ወገኖቻችን የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻለን። በሕዝባችን ላይ የደረሰው ከፍተኛ ጉዳት በገለልተኛ አካል እንዲጣራና ለሕዝቡ ይፋ እንዲደረግ እንጠይቃለን።

2ኛ. በተለያዩ ጸረ-ሲዳማ ኃይሎች በተቀነባበረ ሴራ በሲዳማ እና በሲዳማ ዞን ውስጥ ባሉ ሌሎች ወገኖቻችን  መካከል የጥላቻ ግንብ ለማቆም በተሰራ እኩይ ተግባር ንብረታቸዉን ላጡ ወገኖቻችን እንዲሁም ለደረሰባቸው ጉዳት ኤጀቶ የተሰማዉን ጥልቅ ሃዘን ይገልጻል። ይህንኑ ጉዳይ ገለልተኛ የሆነ አካል እንዲያጣራና ለተጎጅዎች አስፈላጊ ካሳ እንዲከፈል እናሳስባለን። ኤጄቶም ከማህበረሰቡ ጋር በመሆን ወገኖቻችን በፍጥነት ወደ መደበኛ ኑሮ አቸው እንዲመለሱ ጠንክሮ እንደሚሰራ እናሳውቃለን።

3ኛ. መንግስት በሲዳማ ሕዝብ ላይ የአፈናና ግድያ ወንጀል ለመፈጸም የመረጃ ልውውጥ መረቦችን ከአገልግሎት ውጪ በማድረግ፣ በአስቸኳይ አዋጅ ስም ዳር ድንበር የሚጠብቀዉን ወታደር በማዝመት በሕዝቡ ላይ እየወሰደ ያለውን የጭካኔ ተግባር በጽኑ እናወግዛለን። ሕዝቡ ሰላማዊ የዕለት ተዕለት ኑሮውን ተረጋግቶ ማካሄድ እንዲችል ወታደሩ ባአስቸኳይ ዞኑን ለቆ እንዲወጣ እንጠይቃለን።

4ኛ. መንግስት የሚቆጣጠራቸዉ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ሚዛናዊ የሆነ መረጃ ለሕዝቡ እንዲያቀርቡ እየጠየቅን ሚዛናዊነት የጎደለውን ዘገባ በማቅረብ በሲዳማና በሌሎች ህዝቦች መካከል ከፍተኛ ጥላቻ እንዲቀሰቀስ ለአገራዊ አንዲነቱም አደጋ የሚፈጥሩ መረጃወችን ከማሰራጨት እንዲታቀቡ አጥብቀን እንጠይቃለን። ለሕዝብ ሚዛናዊ መረጃ የሚያቀርበው ብቸኛው የሲዳማ ሚዲያ ኔትወርክ (SMN) ስራ እንዲያቋርጥ በማድረግ እና የተቋሙን ስራ አስክያጆች በማሰር የሕዝቡን መረጃ የማግኘት መብት  በመገደብ በመንግስት የተፈጸመውን አስጸያፍ ወንጀል አጥብቀን እንቃወማለን።

5ኛ. መንግስት የሕዝቡን ጥያቄ በማስተጋባታቸው ያሰራቸውን ምሁራን፣ የሚድያ የስራ ሀላፊወች፣ የመብት ተሟጋቾች እና የኤጄቶ እንቅስቃሴ አባላትን በአስቸኳይ እንዲፈታ አበክረን እንጠይቃለን።

6ኛ.  የሲዳማ ሕዝብ ለዘመናት ዋጋ የከፈለበትንና ራሱን በራሱ ለማስተዳደር የወሰነበትን ውሳኔ ምርጫ ቦርድ ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ የሚጠበቅበትን ሕዝበ ውሳኔ እንዲያደርግ በአጽንኦት እናስገነዝባለን። ምርጫ ቦርዱ በህግ ከተሰጠው ሀላፊነት ውጪ ለአሻጥር ፖለቲካ በር በመክፈት ዳግም ለሕዝባችን የእልቂትና የሰቆቃ መንስኤ ከመሆን እንዲቆጠብ አጥብቀን እናሳስባለን።

7ኛ. አሁን ያለው የኤጄቶ ትውልድ ለሲዳማ ነጻነት የሚታገል የመጨረሻ ትውልድ  መሆኑ እንዲታወቅ ይገባል። የኤጄቶን ፍጹም ሰላማዊ ትግል የሕዝቡ ህገመንግስታዊ መብት እስክረጋገጥ ድረስ የሚገታ ምድራዊ ኃይል እንደማይኖር ልናስገነዝብ እንወዳለን። በመንግስት እና ጸረ-ህብረ ብሄራዊ ፌዴራላዊ ስርዓት ኃይሎች አማካኝነት የሚገታ የኤጄቶ እንቅስቃሴ ስለማይኖር  የወጣቱን ሰላማዊ የትግል አማራጭ ለመዝጋት የሚወሰደው ማንኛውም እርምጃ በአስቸኳይ እንዲቆም አጥብቀን እንጠይቃለን።

ኤጄቶ

ሐምሌ 29, 2011

ሲዳማ ሐዋሳ ኢትዮጵያ

የሲዳማ ዳያስፖራ ማህበር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሰጠው መግለጫ!

የሲዳማ ሕዝብ በህገ መንግስቱ የተደነገገውን ራስን በራስ የማስተዳደር የመብት ጥያቄ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ መጠየቁ ይታወሳል። ይሁን እንጂ መንግስት ለሕዝባዊ ጥያቄ ተገቢ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በተለያዩ መንገዶች ጥያቄውን ለመቀልበስ ጥረት ስያደርግ ቆይቷል። የሕዝቡን ሰላማዊ አካሄድ ችላ በማለት የሲዳማን ሕዝብ ከሌላው ወገን ለመነጠል በማሰብ የፕሮፓጋንዳ ስራ ስሰራና ተመሳሳይ ስራ የሚሰሩ አካላትን ስያበረታታ ኖሯል። የሲዳማ ሕዝብ ጥያቄውን በመጠየቁ ብቻ የሚደረስበትን በደል፣ ዛቻ፣ ማስፈራርያ፣ ታሪክ ማጠልሸት እና፣ የአንድነት አፍራሽ ተደርጎ እንዲታይ መደረጉ እንዲቆምና ከሚደርስበት ጥቃት ከለላ እንዲደረግለት ሕዝቡ በተደጋጋሚ ለመንግስት አቤቱታ ስያሰማ ሰነባብቷል። ሆኖም ግን መንግስት ዝምታ ከመምረጡም ባሻገር ምርጫ ቦርድና መንግስታዊ ሚድያዎች ድርጊቶቹን የበለጠ ስያስተጋቡ እንዲሁም መንግስት በፖርላማ በገዛ ሕዝቡ ላይ ይፋዊ ጦርነት ስያውጅ ተደምጧል። ይህንን ተከትሎ መንግስት በዛቻው መሰረት የሲዳማን ሕዝብ በጦር ወረራ እንዲደመስስ፣ የለውጥ ሀይል የሆነውን ወጣት ከማወያየት ይልቅ ባልሰሩት ወንጀል እንዲከስና፣ ከምድር እንድያጠፋላቸው የሚማጸኑ አከላትም ተስተውሎዋል።

መንግስት ለሕዝብ ጥያቄ ተገብውን ምላሽ ለመስጠት የማይቻልባቸውን ሁኔታዎች በዝርዝር ከሕዝቡ ጋር ከመወያየት ይልቅ የእነዚህን ሀይሎች ምክር ተግባራዊ ለማድረግ በቆረጠው መሰረት በወቅቱ ከምርጫ ቦርድ የተሰጠው ግልጽ ያልሆነ መግለጫ እና የህገ መንግስታዊ ጊዜ ገደብ በመጠናቀቁ ምን መደረግ እንደሚገባው ለመነጋገር ወደ ሕዝብ መሰሰብያ ስፍራ ጉዱማሌ በሚያመራው ህዝብ ላይ ወታደሮች በከፈቱት የተኩስ እሩምታ እና ይህንን ተከትሎ በተነሳው አለመረጋጋት መንግስት ባልታጠቀና ሰላማዊ የሲዳማ ህዝብ ላይ በወሰደው ወታደራዊ እርምጃ በርካታ ዜጎች ለሞት፣ለአካል ጉዳት፣ ለንብረት ውድመት ተዳርገዋል። እነዚህ ጉድዳዮችን አስመልክቶ በጁላይ 27/2019 ዓ .ም አስቸኳይ ስብሰባ ያደረገው በውጪ የሚኖሩ የሲዳማ ተወጅ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ማህበር የሚከተለውን ባለ አምስት ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

1. ሰላማዊ የመብት ጥያቄ ባነሱ ሰላማዊ የሲዳማ ብሄር ተወላጆች ላይ መንግስት የወሰደውን ወታደራዊ እርምጃ በጽኑ እናወግዛለን። በጥቃቱም ውድ ህይወታቸውን፣ አካላቸውንና ንብረታቸውን ላጡ ዜጎቻችን፤ እዲሁም ያለ ወንጀላቸው ታስረው ለምንገላቱ ወገኖቻችን እና ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻለን። ለዚህ ሁሉ ድርጊት ከመነሻው እስከመጨረሻው መንግስት እና የህዝብ ሰላማዊ የመብት ጥያቄ እንዳይመለስ በህዝብ ላይ የሀይል እርምጃው እንዲቀጥል ይወተውቱ የነበሩ አካላት ሙሉ ሀላፊነት ይወስዳሉ። የደረሰው ጉዳትም በገለልተኛ አካል ተጣርቶ በዝርዝር ለሕዝብ ይፋ እንዲደረግ አጥብቀን እንጠይቃለን።

2. መንግስት የዜጎችን መረጃ የማግኘት መብት በመደፍጠጥ በመላው ሲዳማ ዞን የኢንቴርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በመዝጋት፣ ብቸኛ የህዝብ ሚድያ የሆነውን የሲዳማ ተሌቪዢን በመዝጋትና የጣቢያውን የስራ ሀላፊወች በማሰር፣ የመብራት አገልግሎት በማቋረጥ ሕዝቡን በጨላማ በመከላከያ ሰራዊት እንዲጨፈጨፍ ያደረገውን እኩይ አረመኔያዊ ተግባር በጽኑ እናወግዛለን። የአገራችን ሕዝቦች በሲዳማ ዞን ስለተከሰተው ትክክለኛና ሚዛናዊ መረጃ ማግኘት እንዲችሉ የሲዳማ ሚድያ ኔትወርክ ቴሌቪዢን ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ እንዲገባ፣ የታሰሩ የጣቢያው ሀላፊወች በአስቸኳይ እንዲፈቱና ገለልተኛ የሆኑ ሚዲያዎችና ተቋማት በነጻነት ገብተው ስለሁኔታው እንዲረዱ በአስቸኳይ ሁኔታወች እንዲመቻቹ አጥብቀን እንጠይቃለን።

3. የሕዝቡን ጥያቄ በሰላማዊ እና በሰለጠነ መንገድ ስያስተጋቡ የቆዩ ምሁራንን ከመደበኛ ስራ ገበታቸው ላይ በማፈናቀል ውሎ አዳራቸው እስር ቤት እንዲሆን የተደረገበት ነውረኛ የመንግስት ተግባር አጥቀን እናወግዛለን። ይህ ድርጊት የአገራችንን የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እርባነ ቢስ የሚያደርግ፣ የሕዝቡን የመኖር ዋስትና የሚያሳጣ፣ ወጣቱ ለአገር ግንባታ ያለውን ፍላጎት የሚያኮስስ የመንግስት የጨለማ ጉዞ አካሄድ ፍንቱዊ አድርጎ የሚያሳይ በመሆኑ በጽኑ እናወግዛለን። ከሰላማዊ የህዝብ የመብት ጥያቄ ጋር በተገናኘ ያለወንጀላቸው ከህግ አግባብ ውጪ የታሰሩ ሁሉ በአስቸኳይ እንዲፈቱ አጥብቀን እናሳስባለን።

4. በሰላማዊ የሲዳማ ሕዝብ ላይ መንግስት በራሱ እና በጸረ ህዝባዊ ስርዓት ናፋቂ ሀይሎች በተቀነባበረ ግርግር የህዝብን ሰላማዊ ጥያቄ ለመደፍጠጥ በወሰደው የተሳሳተ እርምጃ በክሉሉ የታወጀው ወታደራዊ አገዛዝ በአስቸኳይ እንዲነሳ በአጽንኦት እየጠየቅን መንግስት መሰረታዊ የሕዝብ የመናገር፣ የመሰብሰብ፣ ሀሳብን በነፃ የመግለጽ መሰረታዊ መብት እንድጠብቅ እናሳስባላን።

5. ምርጫ ቦርድ በህግ ባልተሰጠው ስልጣን ጣልቃ በመግባት የሕዝቦችን ህገ መንግስታዊ የመብት ጥያቄ ከማደናቀፍ ተቆጥቦ ህዝበ ውሳኔ ለማካሄድ የሚጠበቅበትን የተክኒክ ድጋፍ ብቻ በአስቸኳይ እንዲሰጥ አጥብቀን እንጠይቃለን። ከዚህ በኋላ ሪፈረንደሙን በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ላለማካሄድ በምርጫ ቦርድም ሆነ በማንኛውም አካል የሚደረግ ማደናቀፍያ በሲዳማ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የማይኖረው መሆኑን አጥብቀን እናሳውቃለን።

የሲዳማ ዳያስፖራ ማህበር

ከመላው ዓለም
ጁላይ 29፣ 2019

ከኤጄቶ አጠቃላይ ስብሰባ የተሰጠ የአቋም መግለጫ

ከመላው የሲዳማ አከባቢዎች የተወጣጡ የኤጄቶ ተወካዮች እና የሀዋሳ ከተማ እና አከባቢዋ ኤጄቶች በአንድነት ዛሬ ሰኔ 27 በሀዋሳ ሚልንየም አዳራሽ ባደረጉት አጠቃላይ ስብሰባ የሚከተሉትን የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።

እኛ የሲዳማ ኤጄቶች የሲዳማ ጥያቄና ጥያቄው የሚፈታበት ዴሞክራሲያዊ መንገድ ሀገራዊ ለውጡን በማይናድ መሰረት ላይ የሚገነባና ህብረ ብሄራዊ ፌደራሊዝሙን የሚያጠናክር ኩነት መሆኑን እናምናለን።
ይህን ጥያቄ ላለመለስ የሚደረጉ ማቅማማቶች የለውጥ እሳቤውንና ህገ መንግስቱን በገሀድ እንደመጻረር ይቆጠራል።

ይህ ጥያቄ በአግባቡ ተመልሶ ከውጥረት ማእከልነት ወደ ሰከነ ፖለቲካዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሽግግር የሚወስድ ለውጥ እንዲሆን ለማድረግ የሲዳማ ህዝብ አለምን ያስደመመ ሰላማዊ ትግል ሲያደርግ ከርሟል። ይህ ግዜ ትግላችን ፍሬ አፍርቶ ሊያጎመራ የተቃረበበትና ነጻነታችን እውን ሊሆን ቀናቶች የቀሩበት ግዜ ነው። ከዚህ ግዜ መቃረብ ጋር ተያይዞ ያሉትን ብዥታዎች ለማጥራት በሚከተሉት ጉዳዮች የሚከተሉትን የአቋም መግለጫዎችን እናሰማለን።

1, 11/11/11 የሲዳማ ህዝብ ደቡብ ከሚባል ድሪቶ ውስጥ ለማደር የማይገደድበትና በራሱ እጣ ፈንታ ላይ በራሱ ምክር ቤት ራሱ ብቻ የወሰነበትን ውሳኔ የሚያጸናበት ቀን ነው። ይህን የነጻነት ቀን ለማጨለምና በተንሸዋረረ መልኩ የተረዱ አካላት ይህን ቀን የአለም ፍጸሜ በማስመሰል የሚያሰሙትን ተራ ፕሮፓጋንዳ አምርረን እንቃወማለን።

በዚህች ቀን ነውጥ እንደሚኖር ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች እንደሚፈናቀሉና የመንግስት ተቋማት እንደሚወድሙ የሚዘክሩ አካላት መኖራቸውን እያስተዋልን ሲሆን እንዲህ ያለ እሳቤ 1 ህግን ለማስከበር በሚል ሰበብ ህዝብ እንዲጨፈጨፍና ጥያቄያችን እንዲቀለበስ የቋመጡ ሀይሎች መሆናቸውን ደርሰንበታል። በመሆኑም ለጠላት ሴራና ወጥመድ የሚመች ምንም አይነት አውድ እንዳይኖር አምርረን የምንታገል መሆኑን አጥብቀን የምንታገል ይሆናል።

#2) የሲዳማ ክልል ጥያቄን አስመልክቶ ከየትኛውም አካል የሚሰጥ ኢ-ህገመንግስታዊ፡ምላሽ ምንም አይነት ተቀባይነት አይኖረውም። ይህ በንዲህ እንዳለ ጥያቄያችንንና ውሳኔያችን ለመቀልበስ የሚነዙ ማስፈራሪያዎችና ዛቻዎች የሲዳማን ህዝብ ጥንታዊ የጀግንነት ስነልቦናን በጉልህ ካለመገንዘብ የሚመነጩ ተራ ፉከራዎች እንደሆኑ እንገነዘባለን። ከዚህ ጋር ተያያዞ ከቅርብ ግዜ ወዲህ አንዳንድ ሀይሎች በግንባር ቀደምት ኤጄቶች ላይ ለማድረስ እየሞከሩ ያሉት ዛቻና የግድያ ሙከራ አጥብቀን የምንቃወም ከመሆኑ ባሻገር እንደዚህ አይነት ሙከራዎች ከተደገሙ መዘዛቸው ስለሚከፋ ለማናቸውም ሀይሎች ጠቃሚ ስላልሆኑ እንዳይሞከሩ አናስጠንቅቃለን።

#3) ከቅርብ ግዜ ወዲህ በውስጣዊ እና ውጫዊ ሀይሎች ተዋናይነት እና ደኢህዴናውያን አቀናባሪነት በሲዳማ ህዝብ መካከል ልዩነት እንዳለ አስደርገው ለማስደለቅ የሞከሩት ውሃን የመውቀጥ ዘመቻ ከንቱ ህልም፡መሆኑን ኤጄቶ አበክሮ ያስገነዝባል። የሲዳማ ህዝብ ከአንድ ወንዝ የተቀዳ ከባህር የጠለቀና የሰፈረ አንድ ህዝብ ነው።የሲዳማ ህዝብ በየትኛውም የታሪክ አጋጣሚ አንድነቱን ጥያቄ ውስጥ አስገብቶ አያውቅም። የሲዳማ ህዝብ አንድ ህዝብ ብቻ ሳይሆን አንድ አይነት ህዝብ መሆኑን ዳግም ለአፓርታይድስቶች በሚገባቸው መልኩ ልንነግራቸው እንፈልጋለን።፡

በመጨረሻም የሲዳማ ህዝብ ነጻነቱን እውን ለማድረግ ከርሞ ከከፈለው ዋጋ በላይ አይከፍልም። በባርነትና በውርደት ግዞት ውስጥ ከመኖር የሚበልጥ ዋጋ የሚያስከፍል ነገርም የለም። ህዝባችን ጥያቄውን ዳግም እንዳያነሳ ዛቻና ማስፈራሪያ ባለፈ ታንክና መድፍ የጄት ድብደባና ጂ 3ን ያላስተናገደበት ዘመን የለም። ያልተጋፈጥነው ያልቀመስነው ፈተና ባለመኖሩ ለመጋፈጥ የምንፈራውም ምንም አይነት ምድራዊ መከራ እንደማይኖር ለሚመለከተው ሁሉ ማሳወቅ እንወዳለን።

ኤጀቶ

ሰኔ 27 2011

ሃዋሳ ሲዳማ እትዮጵያ

 

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከሲዳማ ኤጄቶ የተሰጠ መግለጫ

በቀጣይ የትግል አቅጣጫ ላይ በዛሬው ዕለት በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ውይይት ያደረገው ኤጄቶ በዛሬው ዕለት የሚከተለውን መግለጫ አውጥቷል።

1. የሲዳማ ህዝብ አንድነት እና ለትግሉ ያለው ቁርጠኝነት ከመቼውም ግዜ በላይ የጠነከረበት ነው። በግል ፍላጎቶች በተናጡ ጥቂት ቅጥረኞች አማካኝነት አንድነታችን እንደተሸረሸረ ለማስደለቅ ለየት ያለ ሴራ ሲወጠን እንደ ነበር ደርሰንበታል። በዚህ ተራ ህልም የተነሳ የሚከስም ጥያቄ እንደሌለን የትኛውም ውጫዊም ይሁን ውስጣዊ ሀይል ሊገነዘበው ይገባል፡፡

በትክክለኛ ህዝባዊ የሀሳብ ፍጭቶችና ጥያቄዎች መካከል ተቆርቋሪ መስለው በገቡ ሰርጎ ገብ ፖጉማዎችና ተላላኪዎቻቸው የተጀመረ ትግል እንደሌለ ሁሉ የሚከሽፍ ትግል ባለመኖሩ አንድነታችንን ለማናጋት ለሚታትሩ ጥቂት ተለይተው ለሚታወቁ “ወገኖች” በመጨረሻ ሰዓት የመጨረሻ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ማስተላለፍ ይፈልጋል፣

2. በተለያዩ አካባቢዎች የሚነሱ የግልፅነትና የመብት ጥያቄዎች ተገቢና ጠያቂ ዜጋ እንዲፈጠር ከታገልንባቸው ዓላማዎች ውስጥ ዋነኛው በመሆኑ በሚመለከተው አካል እውቅና ተሰጥቷቸው በአግባቡና በመንገዱ ግልፅነት መፍጠርና መመለስ የሚገባቸው በመሆኑ በጥቂት ፖጉማዎች ምክኒያት ህዝባዊ ፍረጃዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙ መልዕክት ተላልፏል። ይህንን ተላልፎ ደምና አጥንት የተከፈለበትን ትግል ለማኮላሸት ለሚሞክር ለሱ ወዮለት!!

3. ክልል ለማወጅ ጥቂት ቀናት በቀሩን በዚህ ጊዜ ብዙ የቤት ስራ አለንና በዚህ ጊዜ ቅንጣት የአተያይም ሆነ የተግባር ስህተቶች ዋጋ የሚያስከፍሉ በመሆናቸው በቀላሉ የሚታለፉ አይሆኑም። በመሆኑም እስከመጨረሻው ሰዓት ሰላማዊና ህጋዊ ትግላችንን እስከ ደም ጠብታ በተቀመረ አኳዃን የምንቀጥል ይሆናል!!

4. ደኢህዴንም ሆነ የፌደራል መንግስት የህዝባችንን ሰላማዊና ህጋዊ ትግል መልክ ለመቀየር ከማሴር ይልቅ ራሳቸውን ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ ሰላማዊ የሽግግር መፍትሄ በማበጀት ለህዝባችን ደህንነትም ሆነ ለራሳቸው ህልውና እንዲሰሩ እናሳስባለን።

በመጨረሻም አንድ መርዶ ለጠላቶቻችን እናረዳቸዋለን! ሲዳማ ለብዙ ዓመታት እንዲፈርስ የተሰራበት አንድነቱን በዚህ አጭር ወራት በማይናድ መሰረት ላይ የገነባ በመሆኑ ደጋግማችሁ ሞክራችሁ እንዳጣችሁት ሁሉ መቼም እንደማይሳካላችሁ ነው!!!

ሰላም ለህዝባችን! ሰላም ለሀገራችን!
ኤጄቶ
15/10/2011 አ/ም
ሀዋሳ – ሲዳማ – ኢትዮጵያ

በመላው ዓለም የሚኖሩ የሲዳማ ተወላጆች በግንቦት 16 1994 ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ ልዩ ስሙ ሎቄ በሚባል አካባቢ የተጨፈጨፉ የሲዳማ ተወላጆችን ለ17ተኛ ጊዜ አስመልክቶ የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

የሲዳማ ሕዝብ ለበርካታ ዓመታት ለነጻነት እና እኩልነት በሚያደርገው ትግል ምክንያት ሲታሰር፣ ሲገደል፣ሲሰደድ፣ሲጨቆንና፣መብቱ ሲገፈፍ ኖሯል። ሕዝቡ ከአጼዎቹ ስርዓት ጀምሮ እስከ አሁኑ አገዛዝ ድረስ መራርና እልህ አስጨራሽ ትግል ማድረጉና እስከ አሁንም እያደረገ መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም የሲዳማ ሕዝብ እራሱን በራሱ ለማስተዳደር የጀመረው ትግል ሰሞነኛ ሳይሆን የቆየና በርካታ ዓመታትን ያስቆጠረ መሆኑ በታሪክ መዛግብት ላይ ሰፍሮ ይገኛል። ይህንንም ትግል በየዘመኑ ያስተባበሩና የመሩ፣ በሂደቱም ውድ ዋጋ የከፈሉ የሕዝቡ የታሪክ ጀግኖች በመሆናቸው በሕዝቡ ዘንድ ለዘመናት ሲታወሱ ይኖራሉ። እነዚህ ጀግኖች ለሲዳማ ነጻነት ካደረጉት ትግል ባሻገር ለአገራችን ነጻነት ያበረከቱት አስተዋጽኦም ቀላል የሚባል አይደለም።

በደርግ ዘመነ መንግስት ወቅትም ነፃነት ናፋቂው የሲዳማ ሕዝብ በተደራጀና በተቀናጀ መንገድ ከፍተኛ ትግል በማድረግ ለእኩልነት፣ለነጻነት እና ለፍትህ ታግሎአል። በወቅቱ ሕዝቡን በማንቃት እና በማደራጀት ባደረገው ትግል የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ወይም ሲአን ለወታደራዊው መንግስት መንኮታኮት ከፍተኛ ድርሻ ከነበራቸው ጥቂት የብሄር ድርጅቶች መካከልም አንዱ ነበር። ድርጅቱ ለሕዝቦች እኩልነት ባደረገው ትግል የተመዘገበውን ውጤት መነሻ በማድረግ በሰላም ለመደራደር በ1983 ዓ. ም ትጥቁን በመፍታት አገር ቤት ቢገባም መንግስት ባደረገው ሸፍጥ ሕዝቡ የትግሉ ውጤት ተቋዳሽ እንዳይሆን ተደርጓል።

በመሆኑም ላለፉት ሀያ ስምንት ዓመታትም በአሁኑ አገዛዘ የሲዳማ ሕዝብ ለነጻነት፣ ለማንነት እና እኩልት ከፍተኛ ዋጋ ሲከፍል ቆይቷል። ከእነዚህ መስዋዕቶች አንዱ የሀዋሳው የሎቄ ጭፍጨፋ ነው፡፡ የቆየውን የህዝቡን በክልል የመደራጀት ጥያቄ እውን ለማድረግ መንግስትን በሰላማዊ መንገድ ለመጠየቅ ግንቦት 16 ቀን 1994 ዓ. ም ሰላማዊ ሰልፍ በወጡ የሲዳማ ተወላጆች ላይ የመንግስት ወታደሮች ባደረሱት ዘግናኝ ጭፍጨፋ ከመቶ በላይ የሚሆኑ ንጹሀን ወገኖቻችን ህይወታቸውን አጥተዋል። ይህን ጭፍጨፋ በወቅቱ የተለያዩ የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና ሚዲያዎች መዘገባቸውም ይታወሳል።

ከእነዚህ ተቋማት በላይ ግን ድርጊቱ በሁሉም የሲዳማ ተዎላጆች ልብ ተመዝግቦ ይገኛል፤ ዕለቱም በሲዳማ ሕዝብ ታሪክ እጅግ አሰቃቂና ጥቁር ቀን በመሆን በታላቅ ሀዘን በየአመቱ ታስቦ ይውላል። የሲዳማ ሕዝብ ዛሬም ቢሆን እራሱን በራሱ ለማስተዳደር በሚያደርገው የትግል ጉዞ ከፍተኛ ዋጋ እየከፈለ ይገኛል። በቅርቡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የሲዳማ ተወላጆች በሰላማዊ መንገድ ድምጻቸውን ማሰማታቸው የሚታወቅ ቢሆንም ፤ መንግስት ሕዝብን ባለማክበርና እውቅናን ባለመስጠት እንዲሁም ህግ ን ባለማክበር በሠላማዊ ትግላችን ላይ ብቻ ሳይሆን በሕዝባችን ላይም ያለውን ንቀት በሚገባ በድጋሚ አሳይቷል። ከዚሁ ጋር በተያያዘና የሎቄውን እልቂት መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ በውጪ የሚኖሩ የሲዳማ ተወላጆች ማህበር የሚከተለውን ባለ ስድስት ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

1ኛ. የሲዳማ ሕዝብ የትግል ዋነኛ መነሻ በሀገራችን የነበሩ መንግስታት ህግን ባለማክበራቸው እና ሰብአዊ መብትን በመጣሳቸው የተፈጸሙ የማንነት በደሎች መሆኑን ህዝባችን በጽኑ ያምናል። የአሁኑም መንግስት የህጎች የበላይ የሆነውን ህገ መንግስት ላለፉት ሀያ ስምንት ዓመታት ባለማክበሩ የህዝባችን እልቂት ዋነኛ መነሻ ሆኗል። ስለዚህ መንግስት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ህገ መንግስቱን እንዲያከብር በአጽዕኖት እናስገነዝባለን። የህዝቦችን እኩልነት እና አንድነት ለመሸርሽር ታስበው ከህገመንግስቱ ተጻረው የሚወጡ አዋጆች እና የፓለቲካ ትዕዛዞችንም አጥብቀን እንቃወማለን፡፡

2ኛ.ህገ መንግስታዊ የሆነውን በክልል የመደራጀት ጥያቄ በሰላማዊ ሰልፍ ለማቅረብ በወጣው ህዝብ ላይ ግንቦት 16 ,1994 ዓ.ም በመንግስት ወታደሮች በተፈጸመ ጭፍጭፋ ከ70 በላይ ንጹህን የሲዳማ ተወላጆች ውድ ህይወታቸውን አጥቷል፡፡ ቤተሰቦቻቸው ተፈናቅሏል፣የሞራል እና የንብረት ውድመት ደርሶባቸዋል። እንዲሁም በርካታ የቤተሰብ ጧሪ ልጆች፣ አባት ፣እናት፣ ወንድም ፣እህት ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ከስራ አለም ጨርሶ ተሰናብተው ለጎዳና ሕይወት ተዳርጓል። ስለዚህ መንግስት የሰብአዊ መብት ጥሰት መሆኑን ተቀብሎ ለእነዚህ ቤተሰቦች በአስቸኳይ የመቋቋሚያ ካሳ እንዲከፍል አጥብቀን እንጠይቃለን።

3ኛ.በሎቄ ጭፍጨፋ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ አመራር በመስጠት፣ በማስፈጸም እንዲሁም ድርጊቱን የተቃወሙ አካላትን በማስፈራራት ፣በማሰርና በማሳደድ ወንጀል የፈፀሙትን ግለሰቦች በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲያቀርብ እንጠይቃለን። ከዚህ በተጨማሪ በህዝባችን ደም እጃቸው የጨቀዩ ግለሰቦችን ዛሬም ቢሆን መንግስት ከአንድ ስልጣን ወደሌላኛው እያሻገረ እየሾማቸው እና እየሸለማቸው የመሄዱ እውነታ ህዝባችንን ያስቆጣ እና መንግስት በህዝባችን ላይ ሲፈጽም የቆየውን ድርጊት መቀጠሉን አመላካች ነው፡፡ ስለሆንም መንግስት በሲዳማ ውድ ልጆች ደም መጫወቱን በማቆም ድርጊቱ እንዳይደገም በሚያስተምር መንገድ ተግባራዊ እርምጃ እንዲወስድ እናሳስባለን፡፡

4ኛ.መንግስት የዜጎችን መብት መጠበቅና ማስተማር እንዲሁም መደገፍ ሲገባው የሲዳማ ህዝብ መብቱን ለመጠየቅ በሰላማዊ መንገድ ላደረገው እንቅስቃሴ እውቅና ከመስጠት ይልቅ የግድያ ፣የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፣ያለአግባብ እስራትና ስደት ህዝባችንን በመዳረጉ፣ አሁንም ቢሆን ይሄው በመቀጠሉ ፣ለሰላማዊ ጥያቄም እውቅናን በመከልከል ሰላማዊ ትግሉን በማንቋሸሽና በማጣጣል የሚያደርገውን ንቀት በመገንዘብ በግልጽ ቋንቋ ህዝቡን ይቅርታ እንዲጠይቅና የመብት ጥያቄውን እንዲመልስ አጥብቀን እናሳስባለን፡፡

5ኛ. በህዝባችን ላይ የተፈጸመ የሎቄ የጅምላ ጭፍጨፋ ዳግም በህዝባችንም ሆነ በሰው ዘር እንዳይፈፀም በጽናት ከህዝባችን ጎን በመሆን የምንታገል ሲሆን ህዝባችን ለትግል የከፈለውን ዋጋ እና የህዝባዊ ትግሉን ዓላማና ግብ ከግምት በማስገባት መንግስት ህዝቡ ለሚያነሳችው ጥያቄ ፍትሃዊ መልስ በአስቸኳይ እንዲመልስ እንጠይቃለን። ያለ አግባብ የተጨፈጨፉ ወገኖቻችንም እንዲታወሱ እና ድርጊቱ እንዳይደገም ለትምህርት በሚሆን መንገድ የመታሰቢያ ሀውልት እንዲቆምላቸው ሁኔታዎች እንዲመቻቹ እንጠይቃለን።

6ኛ. የሲዳማ ህዝብ በሚያደርገው ትግል እንዲሁም በህዝባችን አብሮነትና አቃፊነት ባህል ላይ መንግስት ህግን ባለማክበር እና ባለመፈጸም ለጸረ-ሕብረብሄራዊ-ፌደራልዚም ኃይሎች የሚሰጠውን ድጋፍ እንዲያቆም አበክረን እንጠይቃለን። በአሁኑ ጊዜም ያለአግባብ እየታሰሩ እና ዋጋ እየከፈሉ ያሉ ወገኖቻችንን ድምጽ በመስማት ድርጊቱንም በአስቸኳይ እዲያቆም በአጽንኦት እንጠይቃለን። ከዚህ ጋር በተያያዘ ህዝቡን በሥነልቦና ውጥረት ውስጥ ለመክተት ከአቅም በላይ ባልሆነ ችግር የሀገር መከላከያ ሠራዊትን በሲዳማ ከተሞች በተለይም በሀዋሳ ለማስፈር የሚደረገውን አላስፈላጊ እንቅስቃሴ አጥብቀን እየተቃወምን የመከላከያ ሠራዊቱ ከአካባቢው በአስቸኳይ ለቆ እንድወጣ እንጠይቃለን።

በውጪ ዓለማት የሚኖሩ የሲዳማ ተወላጆች ማህበር ግንቦት 10,2011

Ejjeettote Xawishsha!

Techo Onkoleessa 14, 2011M.D Ejjeettote Miilla Wiinamu Songo Songite Yannate Ikkito Aana Cinaancho Gaamonnni Hasaabbe Aananno Xawishsha Fushshitino.

Techo songonni, xaa yannara Sidaamu daganna ejjeetto illensa qaru sirnyi (Sidaamu Qoqqowi Hajo) wiinni kayissanno gede assinanni loosi hala’ladunni loosamanni noota keentino.

Umihunni, addi addiha xuxxulo sirnya woraddanna quchumma qolle ollollanni Ejjeetto qoqqowu hajo mulaagisse wolere guddanno gede assate looso mixi’ne loobsanni hee’noonnita keentino.

Konnirano, xaa geeshsha waaga baaxxinoonni hajo gafa gantanno gede assate mixonni ejjeettote miilla tidhinokki ajandinni deantannokki gede qaagissitino.

Coy gedera, Sooreessu Gudumaali songo duumba li’middi yiinohu gosoomu polotiki wirro muuxxisanni noota keente, ayno “Ani Sidaamu ejjeettooti!” yaannohu hiikkono gosoomu polotikinni umosi eemadhanno gedenna “Sidaamu Mittimma” calla faarsatenni geerchu qaale agadhanno gede ejjeetto duudhe sokka sayissanno.

Wolewidoonni, akkalu yaadigi amuraatinni addi addi deerrira nooti mitootu mangistete sooreeyye uminsa biilloonye agartanno ejjeetto kalaqidhanni noota buunxoonni.

Togoo ikkitonni halaali sharramaano wolqa daafursate, ejjeettote mereero gibbo kalaqate, ejjeetto giwantino yite coye luushshitannonna Sidaamu xa’mora waa dunate millissanno gashshaano alinni eeli geeshsha noota assinoonni keenonni buunxoonni.

Konnira, togoo gashshaano assootinsanni eemadhitanno gede ejjeetto kaajjishshe sokka sayissanno. Ikka hoogeenna, gooffe daggino yannara Sidaamu xa’mo gufisate addi addi hamaamukko qalanno ajanda dagate giddora wixanni hembeelsannoha gashshootu biso ejjeetto worte la’annokkita seekkite kultanno.

Hatti hakko heedheenna xaa yannara iibbabbe woraddate, zoonetenna quchummate gashshootira hasaawamannori “Ewelo shoomme; Ewelo hoolle!” yaanno duduwooti.

Manna shoomanna shaara Ejjeettote looso di”ikkino. Ejjeetto Sidaamu wolaphora sharrantanno ilamaati ikkinnina kaadirete barcimi agaraano di”ikkitino. “Ewelo shoomme woy ewelo hoolle!” yaanno duduwo FB ikko loosu basera tuqisatenni eemadha hasiissanno.

Togoo duduwo abbe fincannohu Ejjeettimmate wodho gobbaanni ikkinotannna Sidaamu xa’mo gufissanno gaamo ledo lase noosiha ikkinota wodana assa hasiissannote Ejjeettote egensiissanno.

Roorinni, Sidaamu xa’mo Riferendeme agadhinanni wiinni sa’e dagginota seekkine anfe, aantete sharrote raga hasaambe mudhinate dagatenna ejjeettote mittimma hiinxisate assinanni ollanni kutta baalanta seekkine agadha hasiissannota xawissanno.

Wole widoonni, Looqqe Gooffo 17Ki diri qaaggo ayyaanira Harbagoona, Shaafaamo, Bursa, Xexicha, Alatta Wondo, Daalle, Shabbadiibo, Haweela, Tuula lekkatenni tayisse Hawaasa Looqqe iillite wolaphote lubbantu roduuwa qaagate millissanno miilla baalantanna darga dargaho koysidhu roduuwa galattanni, lekkate ha’rinsho beeqqitino miilla dana soorrammohu karsamannonsatano layidhanno gede qaagiissitanno.

Baxxino garinni kayinni, Kuni 17kihu Looqqe Gooffo Qaaggo diri Lubbantu roduuwi saffinota Sidaamu wolapho jeefo iillishate annu annunku uminkera wirro woyyo e’neemmo diro ikka noosita ejjeetto Sidaamu daga baalantera sokka maganyidhanno.

Looqqe Goofo 17ki Diri Qaaggonni aante Onkoleessa 22 nna 23 hossannoti Ficheenkeeti. Konni ayyaanira diinu adawanke hunara qodhe ka’annoha ikkara dandaannota ejjeetto seekkite huwattanno. Kuni Ficheete ayyaani keerunni sa”anno gede baalunku qarqarira noo ejjeetto ayyaana beeqqanno mannira adawu hajo lainohunni huwanyo kalaqqanno gede sokka sayissanno.

Saeno, woraddanna quchummatenni ayyaana ayirrisara Hawaasa daanno manni ledo dagge, dagansanna quchuminsa adawa agadhitanno gara woradunna quchummate gashshooti ledo malantanno gede ejjeetto qaagiissitanno.

Sidaamq, aye gedeno ikkite Fichee qara sirnyanke balaxxe daggurono, baalunku Sidaami illachasi QOQQOWU hajo aana wora hasiissannotanna diinu abbe wixanno biilloontu, woxu, horonna wkl manaadurichinni deama hasiissannosikkita ejjeetto seekkite qaagiissitanno.

Tini Sidaamu Wolaphora Sharrantanno Goofimarchu Ilamaati!

Qeelleemmo!

Ejjeetto
Hawaasa, Sidaama| ETHIOPIA