በሲዳማ ዞን መስተዳደር በጭሬ ወረዳ በደረሰዉ ድንገተኛ አደጋ ላለቁት ወገኖቻችን ከኤጀቶ የተላለፈ የሃዘን መግለጫ

chiretragedy

በሲዳማ ዞን መስተዳደር በጭሬ ወረዳ እና በምዕራብ አርስ ዞን ኔንሴቦ ወረዳ አዋሳኝ በሆኑ ሻካ በሎና ሀሊላ መሎ ቀበሌወች ከትላንት በስትያ ምሽት ከሁለት ሰአት ጀምሮ ለረጅም ሰአታት በጣለው ከባድ ዝናብ ሣብያ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት የ23 ወገኖቻችን ህይወት ማለፉን የተለየዩ የአገር ውስጥና የውጪ የዜና አውታሮች መዘገባቸው ይታወሳል። ይህንን አደጋ በማስመልከት የሲዳማ ኤጄቶወች የሚከተለውን የሃዘን መግለጫ ሰጥቷል።
1. በዚህ አደጋ ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ይገልጻል። እንዲሁም ስለሞቱት እንስሳትና ሰለወደመው ንብረት የተሰማውን ኃዘን እየገለጸ ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ላጡ ወገኖችም መጽናናትን ይመኛል።
2. በአደጋው የተጎዱትን ለመርዳት በሚደረገው ርብርብ ከህብረተሰቡ ጎን በመቆም የሚቻለውን ለማድረግ ዝግጁ እንደሆነ ይገልጻል።
3. ይህ አደጋ የተከሰተው የአካባቢ ጥበቃ በሚገባ ስላልተደረገበትና በቂ መሠረተ ልማት ያልተሠራበት (ለምሳሌ አካባቢው ተዳፋት መሆኑ ብታወቅም መሰል አደጋወችን ለመቋቋም የሚያስችል ኢንፍራስትራክቸር ባለመሠራቱ ) በመሆኑ፤ እርዳታ ለሚፈልጉ ወገኖች እንኳን በፍጥነት መድረስ ባለመቻሉ የጉዳቱ መጠን የከፋ ልሆን ችሏል። ስለሆነም ይህ የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ባለማድረጋቸውና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ለህዝቡ ባለመስጠታቸው ተጠያቂ እንደሆኑ ተገንዝበው አስፈላጊውን ድጋፍና እርዳታ ለህዝቡ እንድያደርጉ ጥርውን ያስተላልፋል።
4. ጉዳዩ በተለያየ በውጪ እና በአገር ውስጥ ሚድያወች በሰፊው ስዘገብ የደቡብ ክልል መንግሥት የህዝብ መረጃ ምንጭ የሆኑት የፌስ ቡክ ገጽ፣ ሬድዮና ተሌቭዥን ስለ አደጋው በጊዜው አለመዘገባቸውና ከሰሚ ሰሚ ዘገባ ይዘው መቅረባቸው የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ መንግሥት ለሲዳማ ህዝብ ያለውን ንቀት የሚያሳይ በመሆኑ የሲዳማ ኤጄቶወች ይህንን በጽኑ ይኮንናሉ።
5. የሲዳማ ህዝብና የሲዳማ ዞን አስተዳደር ይህንን የደኢህዴን እኩይ ሴራ በመረዳት እራሳቸውን ከዚህ እስር ቤት ለማላቀቅ ከኤጄቶወች ጎን ተሰልፈው እንድታገሉ ጥር ያስተላልፋል።
ግንቦት 20 2010
ኤጄቶ
ሓዋሳ