ከሐዋሳ እየተሰማ ያለውን ግርግር በተመለከተ ከሲዳማ ኤጄቶ የወጣ መግለጫ

ccccc

ፊቼ የሠላም በዓል እንጅ የጸብ አይደለም!

በዛሬው ዕለት ደኢህዴን በሠላማዊ መንገድ የሲዳማን የዘመን መለወጫ በዓል ፊቼን ለማክበር በወጣው ሕዝብና ለዘመናት በሠላምና በመከባበር ከብሔሩ ጋር አብሮ ከሚኖሩ የሌሎች ብሔር ተወላጆች፣ በተለይ ከወላይታ ብሔር ተወላጆች ጋር ጸብ ለመጫር መሞከሩንና፣ በተፈጠረው ግጭት የተጎዱ ወገኖች እንዳሉ እየሰማን እንገኛለን። የሲዳማ ኤጄቶወች እንደዚህ ዓይነት ዘመኑ ያለፈበትና የተለመደ ሕዝብን ከሕዝብ ጋር የማጋጨት የኢህአዴግ እኩይ ተግባር እንደማይሠራና የሲዳማ ህዝብም ሆነ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን ተግባር እንድያወግዝ ጥሪውን ያቀርባል።

ደኢህዴን የሲዳማ ሕዝብ እራስን በራስ የማስተዳደር ህገመንግሥታዊ የመብት ጥያቄ እንደገና አንስቶ ባለበት ሰዓት እንደተለመደው እንደዚህ ዓይነት ሴራ በማሴር የሲዳማን ህዝብ ጥያቄ ለማስቆም በኃይል እየሞከረ ይገኛል። ደኢህዴን ይህን በማድረግ፣ በአካባቢው የሚነሱ ግጭቶችን የሚያስቆምና፣ ጸጥታንና ሠላምን ማስጠበቅ የሚችል ብቸኛው አካል እንደሆነ ለማረጋገጥ እየጣረ ይገኛል። ሆኖም ግን ይህ መሰሪ የደኢህዴን ድርጊት የሲዳማን ሕዝብ ልያስቆመው እንደማይችል ልረዱ ይገባል። የሲዳማ ህዝብና ኤጄቶወች የሲዳማ ህዝብ ህገመንግሥታዊ ጥያቄውን ድንጋይ በመወርወር፣ ጎማ በማቃጠል፣ መኪና በመሰባበርና፣ እንዲሁም በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ የሚመለስ እንዳይደል ጽኑ እምነት እንዳለው ልያውቅ ይገባል።

ስለሆነም የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ መንግሥት አገራችን እየተከተለች ባለችው የለውጥ ህደት ተሳታፍ በመሆን ለሲዳማ ህዝብ ጥያቄ ህገመንግሥታዊ ምላሽ በአስቸኳይ እንድሰጡና ከእንዲህ ዓይነት አጉል ሴራ እንድቆጠቡ ጥሪውን ያስተላልፋል።

የሲዳማ ተወላጆችና ኤጄቶወች፣ ይህንን የደኢህዴን እኩይ ተግባር በመገንዘብ፣ ከዚህ ወጥመድ እንድጠነቀቁ፤ ሠላማዊ የፊቼ በዓልን ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በሠላምና በፍቅር አንድ ላይ እንድያከብሩና የተለመደውን ሠላማዊ ትግል በተጠናከረ መልኩ እንድቀጥሉ ጥሪ ያስተላልፋል።

ሰኔ 5 2010
ኤጄቶ
ሐዋሳ