በሲዳማ አካባብ ስላለዉ ወቅታዊ የሃገራችን ሁነታን በተመለከተ ከሲዳማ ኤጀቶ የተሰየጠ መግለጫ

breakingfreeየሲዳማ ሕዝብ በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራና ለሃገርቷ ህገ መንግስት ተገዥ ብቻ ሳይሆን ህገ ምንግስቱን ለማስከበር ብዙ መስዋእትን የከፈለ ሕዝብ ነዉ። ላለፉት ለብዙ ዓመታት ሕገ መንግስቱ ሕዝብን በሚጠቅም መልኩ ሳይሆን ለይስሙላነትና የጥቅቶች መገልገያ ብቻ እንድያገለግል ያደረጉ ስርአቶችን በመታገል እንደለላዉ እትዮጵያዊ ሕዝብ ብዙ መስዋእትን ከፍሎ አሁን ላለንበት ደረጃ አድርሷል።

ያ ሁሉ ታልፎ የህግ የበላይነት እንድከበር ሁሉም ኢትዮጵያዊ ባንድነት በሚሰራበት ባሁኑ ወቅት ጸረ-ሲዳማ ኃይሎች የሲዳማን ሕዝብ ህገ መንግስታዊ ጥያቄን ለመቀልበስ የተለያዩ የጥፋት ኃይሎችን በማሰማራት የሲዳማ ሕዝብ ከተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች መካከል ለዘመናት አብሮ የዘለቀውን አብሮ ተቻችሎና ተፈቃቅሮ የመኖር እሴቶችን ከመናድ አልፈዉ ደም አፋሳሽ ግጭቶችን ለመፍጠር ችለዋል።

ዛረም እነዝህ ኃይሎች ለጥፋት ዓላማቸዉ እጅግ ብዙ ገንዘብ በማፍሰስና የሰዉ ሃይል በማሰማራት በብርቱ እየሠሩ ይገኛሉ። በዝህም ኢትዮጵያዉያን ባብዛኛዉ የሚጠቀምባቸዉን የሃገር ዉስጥና የዉጭ የሚድያ አዉታሮችን በመቆጣጠር በተፈጠሩ ግጭቶች ባብዛኛዉ የተጎዳዉና መስዋእት እየከፈለ ያለዉ የሲዳማ ሕዝብ ሆኖ ሳለ ለሲዳማ ሕዝብ ባላቸዉ ጥልቅ ጥላቻና ንቀት የተነሳ እዉነታዉን ወደ ጎን በመተዉ የተቃራንዉን ወገን የፈጠራ ወሬ እያባዙና እያገዘፉ በመለፈፍ በግልጽ ለሲዳማ ሕዝብ ህገ መንግስታዊ ምላሽ አያስፈልገዉም እስከማለት ደርሰዋል። ይህም የሲዳማን ሕዝብ ሕልዉናና ማንነትን የሚፈታተን ድርግት የሕዝባችንን ትእግስት በእጅጉ እየተፈታተነዉ ይገኛል።

አሁን ስላለዉ ሁኔታን በተመለከተ የሲዳማ ኤጄቶወች የሚከተለውን የአቋም መግለጫ ሰጥተዋል፤

፩.  የሲዳማ ሕዝብ የክልል ጥያቄ የጠየቀዉ ዛረ ሳይሆን ከብዙ ከአመታት በፍት ሲሆን ለሂደቱም ብዙ መስዋእት ከፍሎበት ህገ መንግስቱን ተከትሎ በየደረጃዉ የጸደቀና ሕዝበ ዉሳኔ ማካሀድ ብቻ የቀረዉ ነዉ። ክቡር ጠቅላይ ሚንስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ሐዋሳ በጎበኙ ወቅትም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ሁሉ ጋር ተወያይቶ አሁንም ሕዝብ ሁሉም እንድወያይበት ባሉትም መሰረት የሲዳማ ሕዝብ በሁሉም ወረዳዎችና ቀበለወች ተመካክሮና ተወያይቶ በአንድ ቃል የክልል ጥያቄዉ ባስቸኳይ ተፈጻም እንድሆን ለሚመለከተዉ አካል ዉሳነዉን አስተላልፏል። ይህ የሲዳማ ሕዝብ ድምጽ ህገ ምንግስቱን ተከትሎ ባስቸኳይ ሕዝበ ዉሳነ ተደርጎ ተፈጻም እንድደረግ በአጽንኦት እንጠይቃለን።

፪.  በህወሃት ርዝራዦችና በደህደን የሚመሩት የሲዳማ ጠላቶች ያላቸዉን የአስተዳደራዊ መዋቅርና የሚድያ አዉታሮቻቸዉን በመጠቀም ከሠሩት መጠነ-ሰፍ ወንጄል ከተጠያቅነት ለማምለጥና የሕዝባችንን ጥያቄ ለመቀልበስ የተለያዩ ዘደወችን እየሞከሩ ይገኛሉ። ከነዝህም ዉስጥ ዋናወቹን ወንጀሉን ያቀነባበሩትንና የጸጥታዉ ጉዳይ የሚመለከታቸዉን አካላትን ወደ ጎን በመተዉ በሲዳማ ዉስጥ ያሉ አመራሮችን ብቻ ተጠያቅ ለማድረግ መጣር፡የሲዳማን ሕዝብ ድምጽ ለማፈን መሞከርና የሲዳማ ሕዝብ ከምንግዘዉም በላይ አንድ በሆነበት ወቅት ሕዝቡን ለመከፋፈልና ለቀን ጅቦች ቀዳዳ ለመክፈት የስልጣን ሹም ሽር ለማድረግ ተግተዉ እየሰሩ ይገኛሉ። ደህደን ከተፈጠረ ጊዜ ጀምሮ የሲዳማን ሕዝብ ስገድልና ሲያስገድል የኖሬ መሆኑን የሲዳማ ሕዝብ ጠንቅቆ ስለሚያዉቅና የሲዳማን ሕዝብ ጥያቄ ለማምከን የሚደረግ ማናቸዉም ሙከራ የማይሳካና የቀን ቅዥት መሆኑን ተረድተዉ እጃቸዉን ከሲዳማ ሕዝብ ላይ ባስቸኳይ እንድያነሱ ኤጀቶ አጥብቆ ያሳስባል።

፫.  በሲዳማና በወላይታ ሕዝብ መካከል ግጭት የፈጠሩና ለብዙ ሕይወት መጥፋትና ንብረት መዉደም በስተጀርባ ያሉ አካላት ባስቸኳይ ተጣርቶ ለፍርድ አለመቅረባቸዉ ብቻ ሳይሆን ዛረም ለሽብር ሥራቸዉ ያልተኙና አገራችንን የማተራመስና የዶ/ር አብይን የለውጥ ህደት ለማደናቀፍ በጥፋት ላይ የተሰማሩ በመሆናቸዉ ባስቸኳይ ተይዘዉ ለፍርድ እንድቀርቡ እንጠይቃለን።

፬ . በሲዳማ ሕዝብ ወስጥ ተሰግስጋችሁ በገንዘብና በተለያዬ ጥቅማ ጥቅሞች በመደለል ከሲዳማ ጠላቶች ጋር በማበር የሲዳማን ሕዝብ ህገ መንግስታዊ ጥያቄን ለመቀልበስ የሚታሰሩ ከዝህ ከሞራል ዝቅጠትና ከክህደት ወንጀል ዉስጥ ባስቸኳይ ወጥታችሁ ለማይቀረዉ ለዉጥ ከሕዝቡ ጋር ተቀላቅላችሁ እንድትሰሩና ከተጠያቅነት እንትድኑ ኤጀቶ ጥርዉን ያቀርባል።

የሲዳማ ሕዝብ ህገ መንግስታዊ ጥያቄ ለማደናቀፍ የሚደረግ ምንኛዉም አይነት እንቅስቃሴ ከሥሩ ለማምከን የሲዳማ ኤጀቶ ከሲዳማ ሕዝብ ጎን በመቆም ታርካዊ አደራዉን ይወጣል!

ኤጄቶ
ሐዋሳ – ሲዳማ
ሰኔ 29, 2010