የኤጄቶን መፈራረስ ለማየት ለቋመጣቹ ውጫዊና ውስጣዊ ሟርተኞች

ኤጄቶ በአለት ላይ የተመሠረተ ጠንካራ ህዝባዊ ሀይል ነው ። ኮሽ ባለ ቁጥር ይበታተን ዘንድ በቡና ቤት የተገናኘ ዱሪዬ ስብስብ አይደለም ። የተሰባሰበነው በህዝባችን የቆየ ብሶትና ጭቆናን ማዕከል ባደረገ አጀንዳ ላይ ነው ። የኤጄቶ አላማ የሲዳማ፥ ህዝብ በዚህች ሀገር ውስጥ የሚገባውን ፖለቲካዊ፥ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልዕልና ተጎናጽፎ ከሌሎች ህዝቦች ጋር በመሆን ትልቋን ኢትዮጵያ መገንባት ነው ።

ይህ አጀንዳ እስካለ ድረስ፥ ኤጄቶን መለያየት የሚችል ሀይል የለም ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተወሰኑ ኤጄቶችን ነጥሎ በመምታት የተለየ አጀንዳቸውን ማሳካት የፈለጉ ውጫዊና ውስጣዊ ሀይሎች በስፋት እየተውተረተሩ ይገኛሉ ።

የነዚህ ሀይልች አላማ በሀገር ደረጃ ጎልቶ እየታየ ያለውን የኤጄቶን መልካም ስምና ተግባር ማጠልሸት ሲሆን፤ ከነዚህ ሀይሎች ጀርባ ቀደም ሲል በነበረው ጠያቂ አልባና ልቅ ስርዓት ኋላ ተንጠልጥለው የነበሩ ኮንትሮባንዲስቶች፥ የከሰሩ ካድሬዎች እና አራጣ ደላሎች በስፋት ይታያሉ ።

እነዚህ ሀይሎች ሰሞኑን የነበሩትን ኤጄቶን የማይወክሉ እንቅሰቃሴዎች መሠረት በማድረግ ኤጄቶ መሀል ልዩነት እንዳለ በማስደለቅ አላማቸውን ለማሳካት እየተንቀሱ ይገኛሉ ።

ባሁን ሰዓት ኤጄቶ ከአላማ አንጻር አንድ ነው ። አንድ ማለትና አንድ አይነትነት ደግሞ የተለያዩ ነገሮች ናቸው ። የትኛውም አይነት ማህበራዊ እንቅስቃሴ የሚዳብረው በሀሳብ ልዩነቶች ነው ። የmotive ልዩነት እስከሌለ ድረስ የሀሳብ ልዩነት ሲመጣ መደናገር ከጸረ ዴሞክራሲያዊ አመለካከት የሚመነጭ ፍርሃት ነው ።

በመሆኑም መሠመር ያለበት ጉዳይ “ለምን የሀሳብ ልዩነት ኖረ?” የሚለው ሳይሆን የሀሳብ ልዩነቶችን እንዴት ነው ምናስተናግደው የሚለው ጉዳይ ነው ። ሀሳቦችን በተሻለ ሀሳብ ሞግቶ ፍርዱን ለህዝብ መተው ሲቻል ግለሰቦችን መሠረት ያደረገ ፍረጃና ጥቃት ዘመኑ የሚጠይቀው ተግባር አይደለም ።

የኤጄቶ ቀደሚ መርህ “Halaale” እውነት ነው ። የትኛውም ተግባር የሚመዘነው ከእውነት አንጻር ብቻ ነው ። እውነት የሚገለጠው በመረጃ በጠንካራ አመከንዮ ነው ። ከአመኬንዮ እና ሀሳባዊ ትንተና ውጭ የሆኑ ስሜትን ና ግላዊ ፍላጎትን መሠረት ያደረጉ እንቅስቃሴዎች ድርጊቶች ንግግሮች እና ጽሁፎች የኤጄቶ አቋሞች ሊሆኑ አይችሉም ።,
ሌላው የትኛውም ድርጊት የሚመዘነው ከህዝባችን ሁለንተናዊ ክብርና ጥቅም አንጻር ብቻ እንጂ በግለሰቦች ፍቃድ አይደለም ።

ኤጄቶ የመንግስት ጉዳይ አስፈጻሚ ሳይሆን፥ መንግስትንም ይሁን ሌላውን አካል የህዝባችን ጥቅም ሳይሸራርፍ እንዲከበር አወንታዊ ጫና የሚያደርግ ህዝባዊ ሀይል ነው ። ይህን ያላስተናገደ አካሄድ የኤጄቶ አካሄድ አይደለም ። ከነዚህ መርሆች ያፈነገጠ የትኛውም አካሄድ የሌላ ሀይሎች ተልዕኮ እንጂ የኤጄቶ አጀንዳ ሊሆን አይችልም ። ኤጄቶይዝም ይለምልም!!
#ኤጆቶ
ሀዋሳ፥

ሲዳማ፥

ኢትዮጵያ