የጋዶ 2 ስራ ማቆም አድማ መጠናቀቁን አስመልክቶ ከኤጄቶ የተሰጠ የምስጋና መግለጫ!

ባለፉት ሶስት ቀናት የሥራ ማቆም አድማ በሲዳማ ኤጄቶ ታውጆ እንደነበር ይታወሳል። አድማውም በሁሉም ሲዳማ ወረዳዎች በተሳካ ሁኔታ ተደርጓል።

አንዳንድ ፀረ-ህዝብ ተቋማትና ድርጅቶች አድማውን ለማስተጓጎል ቢሞክሩም። ወጣም ወረደ አድማው ትናንት ማምሻውን ተጠናቋል።

አድማው (Gaado 2) ላይ እንደበፊቱ እግዚአብሔርም ምስክርነቱን በመስጠት በሰላማዊው ሰልፍ ማጠናቀቂያ ላይ ዝናብ ሰጠ። ዛሬም ሲዳማ ላይ ዝናብ በመዝነብ የእውነት አድማ መሆኑን ፈጣሪ ምስክርነቱን፣ ሽማግለዎቹም ምርቃታቸውን ሰጥተው አረጋግጠዋል። ፈጣሪም ቸር ፈራጅ ነውና ምስጋና የሚገባው ነው! ለዚህ የፍትህ ትግል ሰላምም ምስጋና ይገባዋል።
….
“የሲዳማ የረፈረንደም መቆየት የኔም ጉዳይ ነው” በማለት አብሮን የተሰለፉ ድርጅቶችና ተቋማትን እንደኤጄቶ ማመስገን ግድ ይለናል።

በመጀመሪያ ሰላማዊ ትግሉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጉልበቱን አማጦ የተጠቀመው የነጻነት ጮራ ለሆነው ኤጄቶ አባላትና ሲዳማ ህዝብ ምስጋና አቅርበናል።

በመቀጠልም በሲዳማ ምድር በኑሮም ሆነ በንግድ የተሰማሩ ወንድም ህዝቦችን ማመስገን እንፈልጋለን። በተለይ ትኩሳቱ ማዕከል ለሚኖሩ ለሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች።

ሌሎች የመንግስት ተቋማትና ሠራተኞችን፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችንና ሰራተኞችን እንዲሁም ተማሪዎችና መምህራንን ማመስገን እንፈልጋለን።

የሲዳማ ዲያስፖራ ማህበረሰብም እንደወትሮው ላደረጉት የሰለጠነ እንቅስቃሴ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው።

በግል ማህበሣዊ ገጻቸውም ሳይቀር ለተከታዮቻቸው የአድማውን ዓላማና ቀጣይ ውጤት አስመልክቶ ለሰጡት መግለጫ ወንድም ቄሮንና በተለየ ሁኔታ የኦሮሞ አክቲቭስቶችን በዋናነትም አቶ ጃዋር ሞሐመድን ከልብ እናመሰግናለን።

የደኢህዴን ባርነት አንገሽግሾአቸው የሲዳማን መናቅና መረገጥ ፊለፊት በመቃወም የደኢህደንን ልብ የሰበሩትን የወረዳዎችና የመምሪያዎች ካድሬ አባላትን ሳናመሰግናቸው አናልፍም። ምንም እነሱም የጋዶ አባላት ቢሆኑም።

በሲዳማ ውስጥ የሚፎካከሩና ሀገር በቀል የሆኑ ፓርትዎችም ከህዝብ ድምጽና ቅሬታ ጋር በመሆናቸው ኩራት ተሰምቶናል።

የሥራ ማቆም አድማውንም ባልተበረዘና በተገለጸው ልክ ለኢትዮጵያ ህዝብና ደጋፊዎቻችን የቀጥታ ሽፋን ለሰጡ ሚዲያ ተቋማት ምስጋናችን የላቀ ነው። በተለይ OMN ውለታው የሚረሳ አይደለም። EBC, FANA, WALTA፣ OBS እና ሲዳማ ቲቪን እንድሁም ለዓለም ህዝብ ያሰማው BBC እናመሰግናለን።

በመጨረሻም የህብረተሰቡ ደህንነት እንዲጠበቅ የበኩላቸውን የተወጡትን በአድማው ክልል ወሰን የነበሩ ፖሊስ አካላትንና ግለሰቦችን ማመስገን ይፈልጋል።

በተቃራኒው ደግሞ ስራ ለመዝጋት የተገራገሩና ኋላም ለመዝጋት የሞከሩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀዋሳ ዋናው መስራየ ቤትና ሁለት ቅርንጫፎቹ ናቸው።

የሀዋሳ ኢንዲስትሪ ፓርክ የተወሰኑ ብሎኮችም ለአብነት ሼድ 17 የመሰሳሰሉት ከአሰሪ ከአቶ አንዱዓለም አለባቸውን ጨምሮ ሥራ ለመስራት ጥረዋል።

ጸረ-ህዝብነቱን በማመሳከር እየቀጠለ ያለው ኢሳት ቴሌቪዥን አድማውን ሚዛናዊነቱን በማጣመምና በስድብ ዘግቧል። የኢሳት ጋዘጤኞች ሀዋሳ ከተማ እንዳይገቡ በመከለከላቸውም ለብቀላ የሰሩት ዘመቻ እንደሆነም ኤጄቶ ያምናል።

ሙሉ በሙሉ ደግሞ ደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት አለመዝጋቱን አረጋግጠናል። በፈደራልና ልዩ ኃይል መከታም መተመተማመኑን ተመልክቷል። በእርግጥም በጋዶ 2 ምንም እርምጃ ለመውሰድ አቋም ስላልነበረ መረጃ ተይዞ ታልፎለታል። ይህ ደግሞ በጣቢያው የሚጠቀመውን የሲዳማ ቴሌቪዥን አይመለከትም እሱና ሰራተኞቹ ዘግተው ውሎአልና።

ምንም ያህል የክልል መስሪያ ቤት ቢሆንም የደ/ብ/ብ/ህ/ክልላዊ መንግስት ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የአበል እጥረት ስላጋጠመው አድማውን መቀላቀል አልፈለገም።

የሙት መንፈስ የሆነው የአንዳንድ የፈዴራል ፖሊስና የፈራሹ ክልል ልዩ ሀይል በሰላማዊ ቤተሰብ ላይ በወሰዱት እርምጃም በሰው አካል ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ማድረስ ችለዋል። የዚህ ሱስ ቀጣይ አካል የሆነውም የአድማውን ቀን ለማሳጠር በደቡብ ቴሌቪዥን ቀርቦ የሰጡት የማስፈራራየ መግለጫ የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ እምነት በማጣቱ ሳይሳካላቸው አድማው ቀጥሎ በተባለው መንገድ ተጠናቋል።

ገጠር ወረዳዎች ላይ ግን የሚሰማቸው እንኳን አልነበረም አይኖርምም። ከነዚህ መግለጫ ሰጪዎችም ውስጥ ተገድደው መግለጫ የሰጡም እንዳሉ አረጋግጠን Bado ብለን አልፈናል።

ለዚህ ሁሉ የረፈረንደም ቀን ተቆርጦ የማይነገር ከሆነ ሰላማዊ እርምጃ ልወሰድ እንደሚወሰድ
ግንዛቤ ውስጥ ይገባል። ለባንኩ ተጠቃሚን ሌላ ባንክ አማራጭ ማስቀየስ ያስተምራቸዋል። ሌላውንም አስተማሪና የተጠና የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ ኤጄቶ አቅምም እውቀትም አለው።

የሚመለከተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤትና የደ/ብ/ብ/ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ጉዳዪን አስመልክቶ ምንም ያሉት ነገር ባይኖርና ሰላማዊ ግፍቱ ራስ ምክር ቤቶች እስከመወሰን ድረስ ይቀጥላል።

ይህ ሁሉ ሆኖ ግን የረፈረንደም ቀን ተወስኖ ለሲዳማ ህዝብ ይፋ የማደረግ ከሆነ የጠለቀና አስከፊ ሰላማዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ከወዲሁ ይመዘገብልን።

ጋዶ 3 በቅርብ እንዲታወጅ #የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት እየገፋፋን መሆኑንም ልብ ብላችሁ ጋዶው እንዲቋረጥ ቀኑ እንዲገለጥ የድርሻችሁን እንድትወጡ ኤጄቶ ጥሪውን ያቀርባል።

“ይህ ትውልድ ለሲዳማ ነጻነት የሚታገል የመጨረሻው ትውልድ ነው” ኤጄቶ

ኤጄቶ

ሀዋሳ፣ ሲዳማ፣ ኢትዮጵያ
መጋብት 7/2011 ዓ.ም