Category Archives: An Update

የሲዳማ ዳያስፖራ ማህበር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሰጠው መግለጫ!

የሲዳማ ሕዝብ በህገ መንግስቱ የተደነገገውን ራስን በራስ የማስተዳደር የመብት ጥያቄ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ መጠየቁ ይታወሳል። ይሁን እንጂ መንግስት ለሕዝባዊ ጥያቄ ተገቢ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በተለያዩ መንገዶች ጥያቄውን ለመቀልበስ ጥረት ስያደርግ ቆይቷል። የሕዝቡን ሰላማዊ አካሄድ ችላ በማለት የሲዳማን ሕዝብ ከሌላው ወገን ለመነጠል በማሰብ የፕሮፓጋንዳ ስራ ስሰራና ተመሳሳይ ስራ የሚሰሩ አካላትን ስያበረታታ ኖሯል። የሲዳማ ሕዝብ ጥያቄውን በመጠየቁ ብቻ የሚደረስበትን በደል፣ ዛቻ፣ ማስፈራርያ፣ ታሪክ ማጠልሸት እና፣ የአንድነት አፍራሽ ተደርጎ እንዲታይ መደረጉ እንዲቆምና ከሚደርስበት ጥቃት ከለላ እንዲደረግለት ሕዝቡ በተደጋጋሚ ለመንግስት አቤቱታ ስያሰማ ሰነባብቷል። ሆኖም ግን መንግስት ዝምታ ከመምረጡም ባሻገር ምርጫ ቦርድና መንግስታዊ ሚድያዎች ድርጊቶቹን የበለጠ ስያስተጋቡ እንዲሁም መንግስት በፖርላማ በገዛ ሕዝቡ ላይ ይፋዊ ጦርነት ስያውጅ ተደምጧል። ይህንን ተከትሎ መንግስት በዛቻው መሰረት የሲዳማን ሕዝብ በጦር ወረራ እንዲደመስስ፣ የለውጥ ሀይል የሆነውን ወጣት ከማወያየት ይልቅ ባልሰሩት ወንጀል እንዲከስና፣ ከምድር እንድያጠፋላቸው የሚማጸኑ አከላትም ተስተውሎዋል።

መንግስት ለሕዝብ ጥያቄ ተገብውን ምላሽ ለመስጠት የማይቻልባቸውን ሁኔታዎች በዝርዝር ከሕዝቡ ጋር ከመወያየት ይልቅ የእነዚህን ሀይሎች ምክር ተግባራዊ ለማድረግ በቆረጠው መሰረት በወቅቱ ከምርጫ ቦርድ የተሰጠው ግልጽ ያልሆነ መግለጫ እና የህገ መንግስታዊ ጊዜ ገደብ በመጠናቀቁ ምን መደረግ እንደሚገባው ለመነጋገር ወደ ሕዝብ መሰሰብያ ስፍራ ጉዱማሌ በሚያመራው ህዝብ ላይ ወታደሮች በከፈቱት የተኩስ እሩምታ እና ይህንን ተከትሎ በተነሳው አለመረጋጋት መንግስት ባልታጠቀና ሰላማዊ የሲዳማ ህዝብ ላይ በወሰደው ወታደራዊ እርምጃ በርካታ ዜጎች ለሞት፣ለአካል ጉዳት፣ ለንብረት ውድመት ተዳርገዋል። እነዚህ ጉድዳዮችን አስመልክቶ በጁላይ 27/2019 ዓ .ም አስቸኳይ ስብሰባ ያደረገው በውጪ የሚኖሩ የሲዳማ ተወጅ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ማህበር የሚከተለውን ባለ አምስት ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

1. ሰላማዊ የመብት ጥያቄ ባነሱ ሰላማዊ የሲዳማ ብሄር ተወላጆች ላይ መንግስት የወሰደውን ወታደራዊ እርምጃ በጽኑ እናወግዛለን። በጥቃቱም ውድ ህይወታቸውን፣ አካላቸውንና ንብረታቸውን ላጡ ዜጎቻችን፤ እዲሁም ያለ ወንጀላቸው ታስረው ለምንገላቱ ወገኖቻችን እና ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻለን። ለዚህ ሁሉ ድርጊት ከመነሻው እስከመጨረሻው መንግስት እና የህዝብ ሰላማዊ የመብት ጥያቄ እንዳይመለስ በህዝብ ላይ የሀይል እርምጃው እንዲቀጥል ይወተውቱ የነበሩ አካላት ሙሉ ሀላፊነት ይወስዳሉ። የደረሰው ጉዳትም በገለልተኛ አካል ተጣርቶ በዝርዝር ለሕዝብ ይፋ እንዲደረግ አጥብቀን እንጠይቃለን።

2. መንግስት የዜጎችን መረጃ የማግኘት መብት በመደፍጠጥ በመላው ሲዳማ ዞን የኢንቴርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በመዝጋት፣ ብቸኛ የህዝብ ሚድያ የሆነውን የሲዳማ ተሌቪዢን በመዝጋትና የጣቢያውን የስራ ሀላፊወች በማሰር፣ የመብራት አገልግሎት በማቋረጥ ሕዝቡን በጨላማ በመከላከያ ሰራዊት እንዲጨፈጨፍ ያደረገውን እኩይ አረመኔያዊ ተግባር በጽኑ እናወግዛለን። የአገራችን ሕዝቦች በሲዳማ ዞን ስለተከሰተው ትክክለኛና ሚዛናዊ መረጃ ማግኘት እንዲችሉ የሲዳማ ሚድያ ኔትወርክ ቴሌቪዢን ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ እንዲገባ፣ የታሰሩ የጣቢያው ሀላፊወች በአስቸኳይ እንዲፈቱና ገለልተኛ የሆኑ ሚዲያዎችና ተቋማት በነጻነት ገብተው ስለሁኔታው እንዲረዱ በአስቸኳይ ሁኔታወች እንዲመቻቹ አጥብቀን እንጠይቃለን።

3. የሕዝቡን ጥያቄ በሰላማዊ እና በሰለጠነ መንገድ ስያስተጋቡ የቆዩ ምሁራንን ከመደበኛ ስራ ገበታቸው ላይ በማፈናቀል ውሎ አዳራቸው እስር ቤት እንዲሆን የተደረገበት ነውረኛ የመንግስት ተግባር አጥቀን እናወግዛለን። ይህ ድርጊት የአገራችንን የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እርባነ ቢስ የሚያደርግ፣ የሕዝቡን የመኖር ዋስትና የሚያሳጣ፣ ወጣቱ ለአገር ግንባታ ያለውን ፍላጎት የሚያኮስስ የመንግስት የጨለማ ጉዞ አካሄድ ፍንቱዊ አድርጎ የሚያሳይ በመሆኑ በጽኑ እናወግዛለን። ከሰላማዊ የህዝብ የመብት ጥያቄ ጋር በተገናኘ ያለወንጀላቸው ከህግ አግባብ ውጪ የታሰሩ ሁሉ በአስቸኳይ እንዲፈቱ አጥብቀን እናሳስባለን።

4. በሰላማዊ የሲዳማ ሕዝብ ላይ መንግስት በራሱ እና በጸረ ህዝባዊ ስርዓት ናፋቂ ሀይሎች በተቀነባበረ ግርግር የህዝብን ሰላማዊ ጥያቄ ለመደፍጠጥ በወሰደው የተሳሳተ እርምጃ በክሉሉ የታወጀው ወታደራዊ አገዛዝ በአስቸኳይ እንዲነሳ በአጽንኦት እየጠየቅን መንግስት መሰረታዊ የሕዝብ የመናገር፣ የመሰብሰብ፣ ሀሳብን በነፃ የመግለጽ መሰረታዊ መብት እንድጠብቅ እናሳስባላን።

5. ምርጫ ቦርድ በህግ ባልተሰጠው ስልጣን ጣልቃ በመግባት የሕዝቦችን ህገ መንግስታዊ የመብት ጥያቄ ከማደናቀፍ ተቆጥቦ ህዝበ ውሳኔ ለማካሄድ የሚጠበቅበትን የተክኒክ ድጋፍ ብቻ በአስቸኳይ እንዲሰጥ አጥብቀን እንጠይቃለን። ከዚህ በኋላ ሪፈረንደሙን በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ላለማካሄድ በምርጫ ቦርድም ሆነ በማንኛውም አካል የሚደረግ ማደናቀፍያ በሲዳማ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የማይኖረው መሆኑን አጥብቀን እናሳውቃለን።

የሲዳማ ዳያስፖራ ማህበር

ከመላው ዓለም
ጁላይ 29፣ 2019

ከኤጄቶ አጠቃላይ ስብሰባ የተሰጠ የአቋም መግለጫ

ከመላው የሲዳማ አከባቢዎች የተወጣጡ የኤጄቶ ተወካዮች እና የሀዋሳ ከተማ እና አከባቢዋ ኤጄቶች በአንድነት ዛሬ ሰኔ 27 በሀዋሳ ሚልንየም አዳራሽ ባደረጉት አጠቃላይ ስብሰባ የሚከተሉትን የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።

እኛ የሲዳማ ኤጄቶች የሲዳማ ጥያቄና ጥያቄው የሚፈታበት ዴሞክራሲያዊ መንገድ ሀገራዊ ለውጡን በማይናድ መሰረት ላይ የሚገነባና ህብረ ብሄራዊ ፌደራሊዝሙን የሚያጠናክር ኩነት መሆኑን እናምናለን።
ይህን ጥያቄ ላለመለስ የሚደረጉ ማቅማማቶች የለውጥ እሳቤውንና ህገ መንግስቱን በገሀድ እንደመጻረር ይቆጠራል።

ይህ ጥያቄ በአግባቡ ተመልሶ ከውጥረት ማእከልነት ወደ ሰከነ ፖለቲካዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሽግግር የሚወስድ ለውጥ እንዲሆን ለማድረግ የሲዳማ ህዝብ አለምን ያስደመመ ሰላማዊ ትግል ሲያደርግ ከርሟል። ይህ ግዜ ትግላችን ፍሬ አፍርቶ ሊያጎመራ የተቃረበበትና ነጻነታችን እውን ሊሆን ቀናቶች የቀሩበት ግዜ ነው። ከዚህ ግዜ መቃረብ ጋር ተያይዞ ያሉትን ብዥታዎች ለማጥራት በሚከተሉት ጉዳዮች የሚከተሉትን የአቋም መግለጫዎችን እናሰማለን።

1, 11/11/11 የሲዳማ ህዝብ ደቡብ ከሚባል ድሪቶ ውስጥ ለማደር የማይገደድበትና በራሱ እጣ ፈንታ ላይ በራሱ ምክር ቤት ራሱ ብቻ የወሰነበትን ውሳኔ የሚያጸናበት ቀን ነው። ይህን የነጻነት ቀን ለማጨለምና በተንሸዋረረ መልኩ የተረዱ አካላት ይህን ቀን የአለም ፍጸሜ በማስመሰል የሚያሰሙትን ተራ ፕሮፓጋንዳ አምርረን እንቃወማለን።

በዚህች ቀን ነውጥ እንደሚኖር ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች እንደሚፈናቀሉና የመንግስት ተቋማት እንደሚወድሙ የሚዘክሩ አካላት መኖራቸውን እያስተዋልን ሲሆን እንዲህ ያለ እሳቤ 1 ህግን ለማስከበር በሚል ሰበብ ህዝብ እንዲጨፈጨፍና ጥያቄያችን እንዲቀለበስ የቋመጡ ሀይሎች መሆናቸውን ደርሰንበታል። በመሆኑም ለጠላት ሴራና ወጥመድ የሚመች ምንም አይነት አውድ እንዳይኖር አምርረን የምንታገል መሆኑን አጥብቀን የምንታገል ይሆናል።

#2) የሲዳማ ክልል ጥያቄን አስመልክቶ ከየትኛውም አካል የሚሰጥ ኢ-ህገመንግስታዊ፡ምላሽ ምንም አይነት ተቀባይነት አይኖረውም። ይህ በንዲህ እንዳለ ጥያቄያችንንና ውሳኔያችን ለመቀልበስ የሚነዙ ማስፈራሪያዎችና ዛቻዎች የሲዳማን ህዝብ ጥንታዊ የጀግንነት ስነልቦናን በጉልህ ካለመገንዘብ የሚመነጩ ተራ ፉከራዎች እንደሆኑ እንገነዘባለን። ከዚህ ጋር ተያያዞ ከቅርብ ግዜ ወዲህ አንዳንድ ሀይሎች በግንባር ቀደምት ኤጄቶች ላይ ለማድረስ እየሞከሩ ያሉት ዛቻና የግድያ ሙከራ አጥብቀን የምንቃወም ከመሆኑ ባሻገር እንደዚህ አይነት ሙከራዎች ከተደገሙ መዘዛቸው ስለሚከፋ ለማናቸውም ሀይሎች ጠቃሚ ስላልሆኑ እንዳይሞከሩ አናስጠንቅቃለን።

#3) ከቅርብ ግዜ ወዲህ በውስጣዊ እና ውጫዊ ሀይሎች ተዋናይነት እና ደኢህዴናውያን አቀናባሪነት በሲዳማ ህዝብ መካከል ልዩነት እንዳለ አስደርገው ለማስደለቅ የሞከሩት ውሃን የመውቀጥ ዘመቻ ከንቱ ህልም፡መሆኑን ኤጄቶ አበክሮ ያስገነዝባል። የሲዳማ ህዝብ ከአንድ ወንዝ የተቀዳ ከባህር የጠለቀና የሰፈረ አንድ ህዝብ ነው።የሲዳማ ህዝብ በየትኛውም የታሪክ አጋጣሚ አንድነቱን ጥያቄ ውስጥ አስገብቶ አያውቅም። የሲዳማ ህዝብ አንድ ህዝብ ብቻ ሳይሆን አንድ አይነት ህዝብ መሆኑን ዳግም ለአፓርታይድስቶች በሚገባቸው መልኩ ልንነግራቸው እንፈልጋለን።፡

በመጨረሻም የሲዳማ ህዝብ ነጻነቱን እውን ለማድረግ ከርሞ ከከፈለው ዋጋ በላይ አይከፍልም። በባርነትና በውርደት ግዞት ውስጥ ከመኖር የሚበልጥ ዋጋ የሚያስከፍል ነገርም የለም። ህዝባችን ጥያቄውን ዳግም እንዳያነሳ ዛቻና ማስፈራሪያ ባለፈ ታንክና መድፍ የጄት ድብደባና ጂ 3ን ያላስተናገደበት ዘመን የለም። ያልተጋፈጥነው ያልቀመስነው ፈተና ባለመኖሩ ለመጋፈጥ የምንፈራውም ምንም አይነት ምድራዊ መከራ እንደማይኖር ለሚመለከተው ሁሉ ማሳወቅ እንወዳለን።

ኤጀቶ

ሰኔ 27 2011

ሃዋሳ ሲዳማ እትዮጵያ

 

Ejjeettote Xawishsha!

Techo Onkoleessa 14, 2011M.D Ejjeettote Miilla Wiinamu Songo Songite Yannate Ikkito Aana Cinaancho Gaamonnni Hasaabbe Aananno Xawishsha Fushshitino.

Techo songonni, xaa yannara Sidaamu daganna ejjeetto illensa qaru sirnyi (Sidaamu Qoqqowi Hajo) wiinni kayissanno gede assinanni loosi hala’ladunni loosamanni noota keentino.

Umihunni, addi addiha xuxxulo sirnya woraddanna quchumma qolle ollollanni Ejjeetto qoqqowu hajo mulaagisse wolere guddanno gede assate looso mixi’ne loobsanni hee’noonnita keentino.

Konnirano, xaa geeshsha waaga baaxxinoonni hajo gafa gantanno gede assate mixonni ejjeettote miilla tidhinokki ajandinni deantannokki gede qaagissitino.

Coy gedera, Sooreessu Gudumaali songo duumba li’middi yiinohu gosoomu polotiki wirro muuxxisanni noota keente, ayno “Ani Sidaamu ejjeettooti!” yaannohu hiikkono gosoomu polotikinni umosi eemadhanno gedenna “Sidaamu Mittimma” calla faarsatenni geerchu qaale agadhanno gede ejjeetto duudhe sokka sayissanno.

Wolewidoonni, akkalu yaadigi amuraatinni addi addi deerrira nooti mitootu mangistete sooreeyye uminsa biilloonye agartanno ejjeetto kalaqidhanni noota buunxoonni.

Togoo ikkitonni halaali sharramaano wolqa daafursate, ejjeettote mereero gibbo kalaqate, ejjeetto giwantino yite coye luushshitannonna Sidaamu xa’mora waa dunate millissanno gashshaano alinni eeli geeshsha noota assinoonni keenonni buunxoonni.

Konnira, togoo gashshaano assootinsanni eemadhitanno gede ejjeetto kaajjishshe sokka sayissanno. Ikka hoogeenna, gooffe daggino yannara Sidaamu xa’mo gufisate addi addi hamaamukko qalanno ajanda dagate giddora wixanni hembeelsannoha gashshootu biso ejjeetto worte la’annokkita seekkite kultanno.

Hatti hakko heedheenna xaa yannara iibbabbe woraddate, zoonetenna quchummate gashshootira hasaawamannori “Ewelo shoomme; Ewelo hoolle!” yaanno duduwooti.

Manna shoomanna shaara Ejjeettote looso di”ikkino. Ejjeetto Sidaamu wolaphora sharrantanno ilamaati ikkinnina kaadirete barcimi agaraano di”ikkitino. “Ewelo shoomme woy ewelo hoolle!” yaanno duduwo FB ikko loosu basera tuqisatenni eemadha hasiissanno.

Togoo duduwo abbe fincannohu Ejjeettimmate wodho gobbaanni ikkinotannna Sidaamu xa’mo gufissanno gaamo ledo lase noosiha ikkinota wodana assa hasiissannote Ejjeettote egensiissanno.

Roorinni, Sidaamu xa’mo Riferendeme agadhinanni wiinni sa’e dagginota seekkine anfe, aantete sharrote raga hasaambe mudhinate dagatenna ejjeettote mittimma hiinxisate assinanni ollanni kutta baalanta seekkine agadha hasiissannota xawissanno.

Wole widoonni, Looqqe Gooffo 17Ki diri qaaggo ayyaanira Harbagoona, Shaafaamo, Bursa, Xexicha, Alatta Wondo, Daalle, Shabbadiibo, Haweela, Tuula lekkatenni tayisse Hawaasa Looqqe iillite wolaphote lubbantu roduuwa qaagate millissanno miilla baalantanna darga dargaho koysidhu roduuwa galattanni, lekkate ha’rinsho beeqqitino miilla dana soorrammohu karsamannonsatano layidhanno gede qaagiissitanno.

Baxxino garinni kayinni, Kuni 17kihu Looqqe Gooffo Qaaggo diri Lubbantu roduuwi saffinota Sidaamu wolapho jeefo iillishate annu annunku uminkera wirro woyyo e’neemmo diro ikka noosita ejjeetto Sidaamu daga baalantera sokka maganyidhanno.

Looqqe Goofo 17ki Diri Qaaggonni aante Onkoleessa 22 nna 23 hossannoti Ficheenkeeti. Konni ayyaanira diinu adawanke hunara qodhe ka’annoha ikkara dandaannota ejjeetto seekkite huwattanno. Kuni Ficheete ayyaani keerunni sa”anno gede baalunku qarqarira noo ejjeetto ayyaana beeqqanno mannira adawu hajo lainohunni huwanyo kalaqqanno gede sokka sayissanno.

Saeno, woraddanna quchummatenni ayyaana ayirrisara Hawaasa daanno manni ledo dagge, dagansanna quchuminsa adawa agadhitanno gara woradunna quchummate gashshooti ledo malantanno gede ejjeetto qaagiissitanno.

Sidaamq, aye gedeno ikkite Fichee qara sirnyanke balaxxe daggurono, baalunku Sidaami illachasi QOQQOWU hajo aana wora hasiissannotanna diinu abbe wixanno biilloontu, woxu, horonna wkl manaadurichinni deama hasiissannosikkita ejjeetto seekkite qaagiissitanno.

Tini Sidaamu Wolaphora Sharrantanno Goofimarchu Ilamaati!

Qeelleemmo!

Ejjeetto
Hawaasa, Sidaama| ETHIOPIA

Ejjeettote Uurrinsha!

Techo Badheessa 17, 2011M.D Ejjeetto Wiinamu Songo Songite, Lamu Sirinyi Aana Aane Nooha Uurrinshate Xawishsha Fushshitino!

1.Layinki gaadi albaanni Deedeni Sidaamu xa’mo gufisate qixxeessino sanade kaiminni aanasi kaajjado qaafo adhinoonniti qaangannite. Konni korinni, Deedeni Sidaamu Zoonenna Hawaasi Quchumi Gashshooti giddo wolqa afi’rannokkiha assine keeshshinonni.

Xaa yannara Deedeni mereerima komite miilla ikkitinori Sidaamu xa’mo aana huluullo kalaqate untanni noo bale suunfe iillinoonni.

Konnira, Sidaamu xa’mo jeefo gansiisate Deedeni buqqisantenni roore, hee’re reyanno qaafo adha hasiissino.

Hee’re reyanno gede assate qara hayyo, miilla aganunni baaxxitanno fushsho ittisanna Deedenita aye songono songa agura hasiissannota hasaambe sumuu yinoommo.

Ikkinohurano, konni aganinni kayinse, Sidaamu Zoonenna Hawaasi Quchumi Deedeni Miilla Aganu Fushsho (መዋጮ) baattannokki gede kaajjinshe sokka sayinsanni qoleno, Deedeni su’minni aye songono songa hasiissannokkita duu’ne xawinseemmo. Ledeno, konni sirnyi gumulo albankeenni Hamusete barra heedhannonke xaphoomu songonni dhaambeemmota ikkitanno.

2. Deedenino ikko ali gashshooti Sidaamu xa’mo injiisaro duumba qolate, woy xiinxallotenni dawarate, hakkiinni sa’uro, keeshshiishate hasatto noonsata ordinsa leellishanno. Tenne mixonsa gafa gansiisate horonsidhanno hayyo giddonni mitte ninke ninkewa mimmito huluullammeemmo ajanda kalaqa ikkinota keennoommo.

Hattenne hexxonsa gafa gansiissate tafa tuqqino garinni anfeno ikko afa hoogatennk yannara meessi manni sada addi addi doogonni feesibuukete aana kayinsanni keeshshinooniti mittimmanke jifate deerra iillitinota masaalloonni.

Konni ka’a kayinni, giddoydi hajo lammeessine, Sidaamu Xa’mo aana calla illachisha hasiissino. Ikkollana, polotiku qiniite adhate amaalamme giddo baandooti aana mitteenni adhinara qaafo agurranna techo barrinni kayinse, meessi manna feesibuukete aana suntannikki gede duu’ne sokka sayinsanni, jaddote korkaatinni coyinsa higgete anga noo mannooti hajo meessa hi’ra e’nikkinni higgete garinni gumulo afidhanno gede xawinsanni, higgete aana hekko kalaqatenni daga hembeelsitanno mannooti eemadhitanno gede egensiinseemmo.

Tini Ilama Sidaamu Qoqqowo Xintate Sharrantanno Goofimarchu Ilamaati!!

Ejjeetto
Hawaasa,

Sidaama

Ethiopia

Songote Woshshatto!

Ejjeettote Miilla Baalaho

Hajo: Dagate Doorshi (Rifereendemete) Sharrote Hayyo Malate.

Lame lamalara albaanni Sidaamu Geerri ledo Sooreessu Gudumaalira malaho songinummoti qaanganite. Hakko korinni, Sidaamu giddoydi adawi harshammi yiino.

Sidaamu Dagoomi Qoqqowo Ikkate guutisa hasiissannonkeri giddo mitte dagate doorshaati woy riferendemete. Iseno hajo la’annonsari tenne te’enne yitukkinni yanna yannitanni no.

Konni daafira, gashshootu hajonkera illacha tuganno gede kaajjinshe qaagiissa hasiissinohura ikkito songote xaande ma’la hasiissino.

Konni daafira, Sanyo Arfaasa 20, 2011 M.D Soodo 2:30 Hawaasa Milineemete harira leelline ma’lineemmo gede duu’ne egensiinseemmo.
Qeelle_Sidaamaho!

Ejjeetto!
Hawaasa, Sidaama,

Itophiya!

referendum

አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ መስከረም 5/2011 ዓ.ም ወደ ፍቅር ከተማችን ውቢቷ ሃዋሳ መምጣት በሚመለከት የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ በጭፍን ጥላቻ ላይ ተመስርቶ ሳይሆን መሬት በረገጠ ሀቅ ነው::

የተቃውሞው መሠረት ምንድነው??

1. ወንጀል የሰራ ግለሰብ እንደ ግለሰብ አግባብነት ባለው ህግ ሊጠየቅ ይችላል: ይገባልም:: ህዝብ ግን እንደ ህዝብ ሊንጓጠጥ: ሊሰደብ: ሊፈረጅ አይችልም::
ነገር ግን የሰብዓዊ መብት ተከራካሪና የአንድነት ሰባኪ እንደሆነ በሚነገርለት ታማኝ በየነ በሚመራው ኢሳት ቴሌቪዥን በዚህ ባላለቀው ዓመት “ምን አለሽ መቲ” እና ሌሎች ፕሮግራሞች ላይ የሲዳማ ህዝብ እንደህዝብ የትግል ታሪክ እንደሌለው ተደርጎ ለዓለም ህዝብ ቀርቧል(ሙሉ ፕሮግራሞቹን በyoutube ያገኙታል); ተሰድቧል; ተንጓጧል::

እነዚህ ፕሮግራሞች በየዋህነት ሳይሆን ታቅደውና በድርጅቱ Editorial Board (ታማኝን ጨምሮ) እየፀደቁ የሚተላለፉ ናቸው:: እንደ ህዝብ ተሰድቦ ለጠየቀው ይፋዊ ቅሬታ እንኳን ምላሽ ያልተሰጠው የሲዳማ ህዝብ ጉዳዮን ያስተባበረን አካል በቀዬው እንኳን ደህና መጣህልን ብሎ መቀበል የሚያስችል የስነልቦና ዝግጅት ላይ አይደለም::

2. የሲዳማ ህዝብ ለዘመናት ሆደ ሰፊ በመሆን ከሌሎች ወንድም ህዝቦች ጋር በአብሮነት ማንነቱን ሰጥቶ የኖረ ትልቅ ህዝብ ለመሆኑ የተለየ ፖለቲካ ፍላጎት የሌለው ንፁህ ሰው ምስክር ነው:: ለዚህም ማሳያ የሀዋሳን ከተማ ብቻ ማየት ተገቢ ነው:: ሁሉም ኢትዮጵያዊ በፍቅር ሰርቶ የገነባት; ያደገባት; የለማባት እና ያለማት ከተማ ናት::

ይህ በእንዲህ እንዳለ ጥቂት ሰይጣናዊ መንፈስ የተጠናወታቸው; ልዮ ፍላጎት ያላቸው እንዲሁም ሰርቶ ከመኖር ይልቅ የአካባቢውን Native ነዋሪ ክብር በማዋረድ; ስብዕና በመንካትና የይየገባኛል ጥያቄዎች በማንሳት የአንድ ወገን ለምድ በመልበስ ህዝብ ከህዝብ ጋር የማጋጨት ስራ በግልፅም በስውርም በህዝብ ውስጥ ተሸሽገው የሚሰሩ ግለሰቦች አሉ::

የነዚህ ወገኖች ፍላጎት የታማኝ ዓላማ ፍቅርና ድጋፍ ሳይሆን ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ በፍጥነት የተመለሰች ከተማችንን በሲዳማ ውስጥ በኢሳት/ታማኝ ላይ ያለውን ቅሬታ ተጠቅሞ መልሶ ለማተራመስ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ::

3. ታማኝ በየነ የፖለቲካ ሰው ባይሆንም በሚደግፈው/በሚያራምደው አሃዳዊ ስርዓት ከሲዳማ ህዝብ ፍላጎትና ስነልቦና ጋር ፈፅሞ አይታረቅም:: የሲዳማ ህዝብ ተቆጥሮ መደመርን እንጂ መዋሃድን የማያምን በመሆኑ; ለዘመናት ሲጠይቅና ዋጋ ሲከፍል የኖረበትን ራስን በራስ የማስተዳደርና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄ ለማሳካት ጫፍ ላይ በደረሰበት ወቅት በመሆኑ ፍፁም ተቃርኖ “ፖለቲካ” አቀንቃኞችን አጀንዳ የማስተናገድ ስነልቦናዊ ዝግጅት ላይ የማይገኝ መሆኑ ነው::

4. ታማኝ እንደማንኛውም ዜጋ በፈለገበት የሃገሪቱ ክፍል የመንቀሳቀስ መብቱን ተጠቅሞ ሃዋሳን የመጎብኘትና የመዝናናት መብት ቢኖረውም ህዝብ ሰብስቦ ግን ለማወያየት የሲዳማን ህዝብ ይሁንታ ማግኘት ይኖርበታል:: የሀዋሳ ከተማ ነዋሪም ህገ-መንግስታዊ መብቱን ተጠቅሞ ህዝባዊ ተቃውሞውን (public protest) አሰምቷል:: ጥቂቶች አጋጣሚውን ለሽብር ለመጠቀም የተንቀሳቀሱ ቢሆንም ታማኝ እንደሚለው ለህዝብ ክብር የሚሰጥ ከሆነ ፍላጎቱን አክብሮ ለዛ የሚመጥንና የሚያግዝ ምክር ለመስጠትና ይቅርታ ለመጠየቅ ካልሆነ በቀር ተቀባይነት አይኖረውም::

ታማኝ የያዘውን ይዞ ወደሃዋሳችን እንዲመጣ ምን ቅድመ-ሁኔታዎችን ያሟላ??
———-%————-%———–%————–%———–
ከላይ የተገፁና ሌሎች ምክኒያቶች እንዳሉ ሆነው ምሁራዊና ርዕዮታዊ የሃሳብ ፍጭት ለማድረግ የሲዳማ ምሁራን በቂ ሲሆኑ ታማኝ ወደሃዋሳ ለመምጣትና ህዝቡን ለማወያየት የሚከተሉትን ቅድመ-ሁኔታዎች አሟልቶ ከህዝብ መታረቅ ይገባዋል:

## በታማኝ በየነና ጓደኞቹ የሚመራውና ለኢትዮጽያ ህዝብ ቆሜያለው የሚለው ኢሳት ቴሌቪዥን የሲዳማ ህዝብ ትልቅ የኢትዮጵያ ህዝቦች አካል እስከሆነ ድረስ ፀረ-ሲዳማ ፕሮፖጋንዳውን በአስቸኳይ እንዲያቆም ማድረግ;

## ከዚህ በፊት ኢሳት ቴሌቪዥን ላሰራጫቸው ፀረ-ሲዳማ ፕሮግራሞች ይፋዊ ይቅርታ በሙሉ ልሳኖቹ መጠየቅና የማካካሻ ፕሮግራም መስራት;

## ወደ ሀዋሳ ከተማ የሚመጣበትን ምክኒያት; የትኛውን የህብረተስብ ክፍል ማግኘት እንደሚፈልግ እና ዝርዝር ፕሮግራም ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላትና ኤጄቶ አስቀድሞ ማሳወቅና ምላሽ ማግኘት;

ይህ ከሆነ የሲዳማና አካባቢው ህዝብ ህገመንግሥቱን መሠረት አድርጎ በመርህ ፖለቲካዊ ውይይት ለማድረግ ብቁና ዝግጁ ነው! !
ጌደ
ሀዋሳ; ሲዳማ; ኢትዮጽያ