Category Archives: Press release

ከኤጄቶ አጠቃላይ ስብሰባ የተሰጠ የአቋም መግለጫ

ከመላው የሲዳማ አከባቢዎች የተወጣጡ የኤጄቶ ተወካዮች እና የሀዋሳ ከተማ እና አከባቢዋ ኤጄቶች በአንድነት ዛሬ ሰኔ 27 በሀዋሳ ሚልንየም አዳራሽ ባደረጉት አጠቃላይ ስብሰባ የሚከተሉትን የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።

እኛ የሲዳማ ኤጄቶች የሲዳማ ጥያቄና ጥያቄው የሚፈታበት ዴሞክራሲያዊ መንገድ ሀገራዊ ለውጡን በማይናድ መሰረት ላይ የሚገነባና ህብረ ብሄራዊ ፌደራሊዝሙን የሚያጠናክር ኩነት መሆኑን እናምናለን።
ይህን ጥያቄ ላለመለስ የሚደረጉ ማቅማማቶች የለውጥ እሳቤውንና ህገ መንግስቱን በገሀድ እንደመጻረር ይቆጠራል።

ይህ ጥያቄ በአግባቡ ተመልሶ ከውጥረት ማእከልነት ወደ ሰከነ ፖለቲካዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሽግግር የሚወስድ ለውጥ እንዲሆን ለማድረግ የሲዳማ ህዝብ አለምን ያስደመመ ሰላማዊ ትግል ሲያደርግ ከርሟል። ይህ ግዜ ትግላችን ፍሬ አፍርቶ ሊያጎመራ የተቃረበበትና ነጻነታችን እውን ሊሆን ቀናቶች የቀሩበት ግዜ ነው። ከዚህ ግዜ መቃረብ ጋር ተያይዞ ያሉትን ብዥታዎች ለማጥራት በሚከተሉት ጉዳዮች የሚከተሉትን የአቋም መግለጫዎችን እናሰማለን።

1, 11/11/11 የሲዳማ ህዝብ ደቡብ ከሚባል ድሪቶ ውስጥ ለማደር የማይገደድበትና በራሱ እጣ ፈንታ ላይ በራሱ ምክር ቤት ራሱ ብቻ የወሰነበትን ውሳኔ የሚያጸናበት ቀን ነው። ይህን የነጻነት ቀን ለማጨለምና በተንሸዋረረ መልኩ የተረዱ አካላት ይህን ቀን የአለም ፍጸሜ በማስመሰል የሚያሰሙትን ተራ ፕሮፓጋንዳ አምርረን እንቃወማለን።

በዚህች ቀን ነውጥ እንደሚኖር ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች እንደሚፈናቀሉና የመንግስት ተቋማት እንደሚወድሙ የሚዘክሩ አካላት መኖራቸውን እያስተዋልን ሲሆን እንዲህ ያለ እሳቤ 1 ህግን ለማስከበር በሚል ሰበብ ህዝብ እንዲጨፈጨፍና ጥያቄያችን እንዲቀለበስ የቋመጡ ሀይሎች መሆናቸውን ደርሰንበታል። በመሆኑም ለጠላት ሴራና ወጥመድ የሚመች ምንም አይነት አውድ እንዳይኖር አምርረን የምንታገል መሆኑን አጥብቀን የምንታገል ይሆናል።

#2) የሲዳማ ክልል ጥያቄን አስመልክቶ ከየትኛውም አካል የሚሰጥ ኢ-ህገመንግስታዊ፡ምላሽ ምንም አይነት ተቀባይነት አይኖረውም። ይህ በንዲህ እንዳለ ጥያቄያችንንና ውሳኔያችን ለመቀልበስ የሚነዙ ማስፈራሪያዎችና ዛቻዎች የሲዳማን ህዝብ ጥንታዊ የጀግንነት ስነልቦናን በጉልህ ካለመገንዘብ የሚመነጩ ተራ ፉከራዎች እንደሆኑ እንገነዘባለን። ከዚህ ጋር ተያያዞ ከቅርብ ግዜ ወዲህ አንዳንድ ሀይሎች በግንባር ቀደምት ኤጄቶች ላይ ለማድረስ እየሞከሩ ያሉት ዛቻና የግድያ ሙከራ አጥብቀን የምንቃወም ከመሆኑ ባሻገር እንደዚህ አይነት ሙከራዎች ከተደገሙ መዘዛቸው ስለሚከፋ ለማናቸውም ሀይሎች ጠቃሚ ስላልሆኑ እንዳይሞከሩ አናስጠንቅቃለን።

#3) ከቅርብ ግዜ ወዲህ በውስጣዊ እና ውጫዊ ሀይሎች ተዋናይነት እና ደኢህዴናውያን አቀናባሪነት በሲዳማ ህዝብ መካከል ልዩነት እንዳለ አስደርገው ለማስደለቅ የሞከሩት ውሃን የመውቀጥ ዘመቻ ከንቱ ህልም፡መሆኑን ኤጄቶ አበክሮ ያስገነዝባል። የሲዳማ ህዝብ ከአንድ ወንዝ የተቀዳ ከባህር የጠለቀና የሰፈረ አንድ ህዝብ ነው።የሲዳማ ህዝብ በየትኛውም የታሪክ አጋጣሚ አንድነቱን ጥያቄ ውስጥ አስገብቶ አያውቅም። የሲዳማ ህዝብ አንድ ህዝብ ብቻ ሳይሆን አንድ አይነት ህዝብ መሆኑን ዳግም ለአፓርታይድስቶች በሚገባቸው መልኩ ልንነግራቸው እንፈልጋለን።፡

በመጨረሻም የሲዳማ ህዝብ ነጻነቱን እውን ለማድረግ ከርሞ ከከፈለው ዋጋ በላይ አይከፍልም። በባርነትና በውርደት ግዞት ውስጥ ከመኖር የሚበልጥ ዋጋ የሚያስከፍል ነገርም የለም። ህዝባችን ጥያቄውን ዳግም እንዳያነሳ ዛቻና ማስፈራሪያ ባለፈ ታንክና መድፍ የጄት ድብደባና ጂ 3ን ያላስተናገደበት ዘመን የለም። ያልተጋፈጥነው ያልቀመስነው ፈተና ባለመኖሩ ለመጋፈጥ የምንፈራውም ምንም አይነት ምድራዊ መከራ እንደማይኖር ለሚመለከተው ሁሉ ማሳወቅ እንወዳለን።

ኤጀቶ

ሰኔ 27 2011

ሃዋሳ ሲዳማ እትዮጵያ

 

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከሲዳማ ኤጄቶ የተሰጠ መግለጫ

በቀጣይ የትግል አቅጣጫ ላይ በዛሬው ዕለት በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ውይይት ያደረገው ኤጄቶ በዛሬው ዕለት የሚከተለውን መግለጫ አውጥቷል።

1. የሲዳማ ህዝብ አንድነት እና ለትግሉ ያለው ቁርጠኝነት ከመቼውም ግዜ በላይ የጠነከረበት ነው። በግል ፍላጎቶች በተናጡ ጥቂት ቅጥረኞች አማካኝነት አንድነታችን እንደተሸረሸረ ለማስደለቅ ለየት ያለ ሴራ ሲወጠን እንደ ነበር ደርሰንበታል። በዚህ ተራ ህልም የተነሳ የሚከስም ጥያቄ እንደሌለን የትኛውም ውጫዊም ይሁን ውስጣዊ ሀይል ሊገነዘበው ይገባል፡፡

በትክክለኛ ህዝባዊ የሀሳብ ፍጭቶችና ጥያቄዎች መካከል ተቆርቋሪ መስለው በገቡ ሰርጎ ገብ ፖጉማዎችና ተላላኪዎቻቸው የተጀመረ ትግል እንደሌለ ሁሉ የሚከሽፍ ትግል ባለመኖሩ አንድነታችንን ለማናጋት ለሚታትሩ ጥቂት ተለይተው ለሚታወቁ “ወገኖች” በመጨረሻ ሰዓት የመጨረሻ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ማስተላለፍ ይፈልጋል፣

2. በተለያዩ አካባቢዎች የሚነሱ የግልፅነትና የመብት ጥያቄዎች ተገቢና ጠያቂ ዜጋ እንዲፈጠር ከታገልንባቸው ዓላማዎች ውስጥ ዋነኛው በመሆኑ በሚመለከተው አካል እውቅና ተሰጥቷቸው በአግባቡና በመንገዱ ግልፅነት መፍጠርና መመለስ የሚገባቸው በመሆኑ በጥቂት ፖጉማዎች ምክኒያት ህዝባዊ ፍረጃዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙ መልዕክት ተላልፏል። ይህንን ተላልፎ ደምና አጥንት የተከፈለበትን ትግል ለማኮላሸት ለሚሞክር ለሱ ወዮለት!!

3. ክልል ለማወጅ ጥቂት ቀናት በቀሩን በዚህ ጊዜ ብዙ የቤት ስራ አለንና በዚህ ጊዜ ቅንጣት የአተያይም ሆነ የተግባር ስህተቶች ዋጋ የሚያስከፍሉ በመሆናቸው በቀላሉ የሚታለፉ አይሆኑም። በመሆኑም እስከመጨረሻው ሰዓት ሰላማዊና ህጋዊ ትግላችንን እስከ ደም ጠብታ በተቀመረ አኳዃን የምንቀጥል ይሆናል!!

4. ደኢህዴንም ሆነ የፌደራል መንግስት የህዝባችንን ሰላማዊና ህጋዊ ትግል መልክ ለመቀየር ከማሴር ይልቅ ራሳቸውን ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ ሰላማዊ የሽግግር መፍትሄ በማበጀት ለህዝባችን ደህንነትም ሆነ ለራሳቸው ህልውና እንዲሰሩ እናሳስባለን።

በመጨረሻም አንድ መርዶ ለጠላቶቻችን እናረዳቸዋለን! ሲዳማ ለብዙ ዓመታት እንዲፈርስ የተሰራበት አንድነቱን በዚህ አጭር ወራት በማይናድ መሰረት ላይ የገነባ በመሆኑ ደጋግማችሁ ሞክራችሁ እንዳጣችሁት ሁሉ መቼም እንደማይሳካላችሁ ነው!!!

ሰላም ለህዝባችን! ሰላም ለሀገራችን!
ኤጄቶ
15/10/2011 አ/ም
ሀዋሳ – ሲዳማ – ኢትዮጵያ

በመላው ዓለም የሚኖሩ የሲዳማ ተወላጆች በግንቦት 16 1994 ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ ልዩ ስሙ ሎቄ በሚባል አካባቢ የተጨፈጨፉ የሲዳማ ተወላጆችን ለ17ተኛ ጊዜ አስመልክቶ የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

የሲዳማ ሕዝብ ለበርካታ ዓመታት ለነጻነት እና እኩልነት በሚያደርገው ትግል ምክንያት ሲታሰር፣ ሲገደል፣ሲሰደድ፣ሲጨቆንና፣መብቱ ሲገፈፍ ኖሯል። ሕዝቡ ከአጼዎቹ ስርዓት ጀምሮ እስከ አሁኑ አገዛዝ ድረስ መራርና እልህ አስጨራሽ ትግል ማድረጉና እስከ አሁንም እያደረገ መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም የሲዳማ ሕዝብ እራሱን በራሱ ለማስተዳደር የጀመረው ትግል ሰሞነኛ ሳይሆን የቆየና በርካታ ዓመታትን ያስቆጠረ መሆኑ በታሪክ መዛግብት ላይ ሰፍሮ ይገኛል። ይህንንም ትግል በየዘመኑ ያስተባበሩና የመሩ፣ በሂደቱም ውድ ዋጋ የከፈሉ የሕዝቡ የታሪክ ጀግኖች በመሆናቸው በሕዝቡ ዘንድ ለዘመናት ሲታወሱ ይኖራሉ። እነዚህ ጀግኖች ለሲዳማ ነጻነት ካደረጉት ትግል ባሻገር ለአገራችን ነጻነት ያበረከቱት አስተዋጽኦም ቀላል የሚባል አይደለም።

በደርግ ዘመነ መንግስት ወቅትም ነፃነት ናፋቂው የሲዳማ ሕዝብ በተደራጀና በተቀናጀ መንገድ ከፍተኛ ትግል በማድረግ ለእኩልነት፣ለነጻነት እና ለፍትህ ታግሎአል። በወቅቱ ሕዝቡን በማንቃት እና በማደራጀት ባደረገው ትግል የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ወይም ሲአን ለወታደራዊው መንግስት መንኮታኮት ከፍተኛ ድርሻ ከነበራቸው ጥቂት የብሄር ድርጅቶች መካከልም አንዱ ነበር። ድርጅቱ ለሕዝቦች እኩልነት ባደረገው ትግል የተመዘገበውን ውጤት መነሻ በማድረግ በሰላም ለመደራደር በ1983 ዓ. ም ትጥቁን በመፍታት አገር ቤት ቢገባም መንግስት ባደረገው ሸፍጥ ሕዝቡ የትግሉ ውጤት ተቋዳሽ እንዳይሆን ተደርጓል።

በመሆኑም ላለፉት ሀያ ስምንት ዓመታትም በአሁኑ አገዛዘ የሲዳማ ሕዝብ ለነጻነት፣ ለማንነት እና እኩልት ከፍተኛ ዋጋ ሲከፍል ቆይቷል። ከእነዚህ መስዋዕቶች አንዱ የሀዋሳው የሎቄ ጭፍጨፋ ነው፡፡ የቆየውን የህዝቡን በክልል የመደራጀት ጥያቄ እውን ለማድረግ መንግስትን በሰላማዊ መንገድ ለመጠየቅ ግንቦት 16 ቀን 1994 ዓ. ም ሰላማዊ ሰልፍ በወጡ የሲዳማ ተወላጆች ላይ የመንግስት ወታደሮች ባደረሱት ዘግናኝ ጭፍጨፋ ከመቶ በላይ የሚሆኑ ንጹሀን ወገኖቻችን ህይወታቸውን አጥተዋል። ይህን ጭፍጨፋ በወቅቱ የተለያዩ የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና ሚዲያዎች መዘገባቸውም ይታወሳል።

ከእነዚህ ተቋማት በላይ ግን ድርጊቱ በሁሉም የሲዳማ ተዎላጆች ልብ ተመዝግቦ ይገኛል፤ ዕለቱም በሲዳማ ሕዝብ ታሪክ እጅግ አሰቃቂና ጥቁር ቀን በመሆን በታላቅ ሀዘን በየአመቱ ታስቦ ይውላል። የሲዳማ ሕዝብ ዛሬም ቢሆን እራሱን በራሱ ለማስተዳደር በሚያደርገው የትግል ጉዞ ከፍተኛ ዋጋ እየከፈለ ይገኛል። በቅርቡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የሲዳማ ተወላጆች በሰላማዊ መንገድ ድምጻቸውን ማሰማታቸው የሚታወቅ ቢሆንም ፤ መንግስት ሕዝብን ባለማክበርና እውቅናን ባለመስጠት እንዲሁም ህግ ን ባለማክበር በሠላማዊ ትግላችን ላይ ብቻ ሳይሆን በሕዝባችን ላይም ያለውን ንቀት በሚገባ በድጋሚ አሳይቷል። ከዚሁ ጋር በተያያዘና የሎቄውን እልቂት መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ በውጪ የሚኖሩ የሲዳማ ተወላጆች ማህበር የሚከተለውን ባለ ስድስት ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

1ኛ. የሲዳማ ሕዝብ የትግል ዋነኛ መነሻ በሀገራችን የነበሩ መንግስታት ህግን ባለማክበራቸው እና ሰብአዊ መብትን በመጣሳቸው የተፈጸሙ የማንነት በደሎች መሆኑን ህዝባችን በጽኑ ያምናል። የአሁኑም መንግስት የህጎች የበላይ የሆነውን ህገ መንግስት ላለፉት ሀያ ስምንት ዓመታት ባለማክበሩ የህዝባችን እልቂት ዋነኛ መነሻ ሆኗል። ስለዚህ መንግስት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ህገ መንግስቱን እንዲያከብር በአጽዕኖት እናስገነዝባለን። የህዝቦችን እኩልነት እና አንድነት ለመሸርሽር ታስበው ከህገመንግስቱ ተጻረው የሚወጡ አዋጆች እና የፓለቲካ ትዕዛዞችንም አጥብቀን እንቃወማለን፡፡

2ኛ.ህገ መንግስታዊ የሆነውን በክልል የመደራጀት ጥያቄ በሰላማዊ ሰልፍ ለማቅረብ በወጣው ህዝብ ላይ ግንቦት 16 ,1994 ዓ.ም በመንግስት ወታደሮች በተፈጸመ ጭፍጭፋ ከ70 በላይ ንጹህን የሲዳማ ተወላጆች ውድ ህይወታቸውን አጥቷል፡፡ ቤተሰቦቻቸው ተፈናቅሏል፣የሞራል እና የንብረት ውድመት ደርሶባቸዋል። እንዲሁም በርካታ የቤተሰብ ጧሪ ልጆች፣ አባት ፣እናት፣ ወንድም ፣እህት ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ከስራ አለም ጨርሶ ተሰናብተው ለጎዳና ሕይወት ተዳርጓል። ስለዚህ መንግስት የሰብአዊ መብት ጥሰት መሆኑን ተቀብሎ ለእነዚህ ቤተሰቦች በአስቸኳይ የመቋቋሚያ ካሳ እንዲከፍል አጥብቀን እንጠይቃለን።

3ኛ.በሎቄ ጭፍጨፋ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ አመራር በመስጠት፣ በማስፈጸም እንዲሁም ድርጊቱን የተቃወሙ አካላትን በማስፈራራት ፣በማሰርና በማሳደድ ወንጀል የፈፀሙትን ግለሰቦች በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲያቀርብ እንጠይቃለን። ከዚህ በተጨማሪ በህዝባችን ደም እጃቸው የጨቀዩ ግለሰቦችን ዛሬም ቢሆን መንግስት ከአንድ ስልጣን ወደሌላኛው እያሻገረ እየሾማቸው እና እየሸለማቸው የመሄዱ እውነታ ህዝባችንን ያስቆጣ እና መንግስት በህዝባችን ላይ ሲፈጽም የቆየውን ድርጊት መቀጠሉን አመላካች ነው፡፡ ስለሆንም መንግስት በሲዳማ ውድ ልጆች ደም መጫወቱን በማቆም ድርጊቱ እንዳይደገም በሚያስተምር መንገድ ተግባራዊ እርምጃ እንዲወስድ እናሳስባለን፡፡

4ኛ.መንግስት የዜጎችን መብት መጠበቅና ማስተማር እንዲሁም መደገፍ ሲገባው የሲዳማ ህዝብ መብቱን ለመጠየቅ በሰላማዊ መንገድ ላደረገው እንቅስቃሴ እውቅና ከመስጠት ይልቅ የግድያ ፣የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፣ያለአግባብ እስራትና ስደት ህዝባችንን በመዳረጉ፣ አሁንም ቢሆን ይሄው በመቀጠሉ ፣ለሰላማዊ ጥያቄም እውቅናን በመከልከል ሰላማዊ ትግሉን በማንቋሸሽና በማጣጣል የሚያደርገውን ንቀት በመገንዘብ በግልጽ ቋንቋ ህዝቡን ይቅርታ እንዲጠይቅና የመብት ጥያቄውን እንዲመልስ አጥብቀን እናሳስባለን፡፡

5ኛ. በህዝባችን ላይ የተፈጸመ የሎቄ የጅምላ ጭፍጨፋ ዳግም በህዝባችንም ሆነ በሰው ዘር እንዳይፈፀም በጽናት ከህዝባችን ጎን በመሆን የምንታገል ሲሆን ህዝባችን ለትግል የከፈለውን ዋጋ እና የህዝባዊ ትግሉን ዓላማና ግብ ከግምት በማስገባት መንግስት ህዝቡ ለሚያነሳችው ጥያቄ ፍትሃዊ መልስ በአስቸኳይ እንዲመልስ እንጠይቃለን። ያለ አግባብ የተጨፈጨፉ ወገኖቻችንም እንዲታወሱ እና ድርጊቱ እንዳይደገም ለትምህርት በሚሆን መንገድ የመታሰቢያ ሀውልት እንዲቆምላቸው ሁኔታዎች እንዲመቻቹ እንጠይቃለን።

6ኛ. የሲዳማ ህዝብ በሚያደርገው ትግል እንዲሁም በህዝባችን አብሮነትና አቃፊነት ባህል ላይ መንግስት ህግን ባለማክበር እና ባለመፈጸም ለጸረ-ሕብረብሄራዊ-ፌደራልዚም ኃይሎች የሚሰጠውን ድጋፍ እንዲያቆም አበክረን እንጠይቃለን። በአሁኑ ጊዜም ያለአግባብ እየታሰሩ እና ዋጋ እየከፈሉ ያሉ ወገኖቻችንን ድምጽ በመስማት ድርጊቱንም በአስቸኳይ እዲያቆም በአጽንኦት እንጠይቃለን። ከዚህ ጋር በተያያዘ ህዝቡን በሥነልቦና ውጥረት ውስጥ ለመክተት ከአቅም በላይ ባልሆነ ችግር የሀገር መከላከያ ሠራዊትን በሲዳማ ከተሞች በተለይም በሀዋሳ ለማስፈር የሚደረገውን አላስፈላጊ እንቅስቃሴ አጥብቀን እየተቃወምን የመከላከያ ሠራዊቱ ከአካባቢው በአስቸኳይ ለቆ እንድወጣ እንጠይቃለን።

በውጪ ዓለማት የሚኖሩ የሲዳማ ተወላጆች ማህበር ግንቦት 10,2011

Ejjeettote Xawishsha!

Techo Onkoleessa 14, 2011M.D Ejjeettote Miilla Wiinamu Songo Songite Yannate Ikkito Aana Cinaancho Gaamonnni Hasaabbe Aananno Xawishsha Fushshitino.

Techo songonni, xaa yannara Sidaamu daganna ejjeetto illensa qaru sirnyi (Sidaamu Qoqqowi Hajo) wiinni kayissanno gede assinanni loosi hala’ladunni loosamanni noota keentino.

Umihunni, addi addiha xuxxulo sirnya woraddanna quchumma qolle ollollanni Ejjeetto qoqqowu hajo mulaagisse wolere guddanno gede assate looso mixi’ne loobsanni hee’noonnita keentino.

Konnirano, xaa geeshsha waaga baaxxinoonni hajo gafa gantanno gede assate mixonni ejjeettote miilla tidhinokki ajandinni deantannokki gede qaagissitino.

Coy gedera, Sooreessu Gudumaali songo duumba li’middi yiinohu gosoomu polotiki wirro muuxxisanni noota keente, ayno “Ani Sidaamu ejjeettooti!” yaannohu hiikkono gosoomu polotikinni umosi eemadhanno gedenna “Sidaamu Mittimma” calla faarsatenni geerchu qaale agadhanno gede ejjeetto duudhe sokka sayissanno.

Wolewidoonni, akkalu yaadigi amuraatinni addi addi deerrira nooti mitootu mangistete sooreeyye uminsa biilloonye agartanno ejjeetto kalaqidhanni noota buunxoonni.

Togoo ikkitonni halaali sharramaano wolqa daafursate, ejjeettote mereero gibbo kalaqate, ejjeetto giwantino yite coye luushshitannonna Sidaamu xa’mora waa dunate millissanno gashshaano alinni eeli geeshsha noota assinoonni keenonni buunxoonni.

Konnira, togoo gashshaano assootinsanni eemadhitanno gede ejjeetto kaajjishshe sokka sayissanno. Ikka hoogeenna, gooffe daggino yannara Sidaamu xa’mo gufisate addi addi hamaamukko qalanno ajanda dagate giddora wixanni hembeelsannoha gashshootu biso ejjeetto worte la’annokkita seekkite kultanno.

Hatti hakko heedheenna xaa yannara iibbabbe woraddate, zoonetenna quchummate gashshootira hasaawamannori “Ewelo shoomme; Ewelo hoolle!” yaanno duduwooti.

Manna shoomanna shaara Ejjeettote looso di”ikkino. Ejjeetto Sidaamu wolaphora sharrantanno ilamaati ikkinnina kaadirete barcimi agaraano di”ikkitino. “Ewelo shoomme woy ewelo hoolle!” yaanno duduwo FB ikko loosu basera tuqisatenni eemadha hasiissanno.

Togoo duduwo abbe fincannohu Ejjeettimmate wodho gobbaanni ikkinotannna Sidaamu xa’mo gufissanno gaamo ledo lase noosiha ikkinota wodana assa hasiissannote Ejjeettote egensiissanno.

Roorinni, Sidaamu xa’mo Riferendeme agadhinanni wiinni sa’e dagginota seekkine anfe, aantete sharrote raga hasaambe mudhinate dagatenna ejjeettote mittimma hiinxisate assinanni ollanni kutta baalanta seekkine agadha hasiissannota xawissanno.

Wole widoonni, Looqqe Gooffo 17Ki diri qaaggo ayyaanira Harbagoona, Shaafaamo, Bursa, Xexicha, Alatta Wondo, Daalle, Shabbadiibo, Haweela, Tuula lekkatenni tayisse Hawaasa Looqqe iillite wolaphote lubbantu roduuwa qaagate millissanno miilla baalantanna darga dargaho koysidhu roduuwa galattanni, lekkate ha’rinsho beeqqitino miilla dana soorrammohu karsamannonsatano layidhanno gede qaagiissitanno.

Baxxino garinni kayinni, Kuni 17kihu Looqqe Gooffo Qaaggo diri Lubbantu roduuwi saffinota Sidaamu wolapho jeefo iillishate annu annunku uminkera wirro woyyo e’neemmo diro ikka noosita ejjeetto Sidaamu daga baalantera sokka maganyidhanno.

Looqqe Goofo 17ki Diri Qaaggonni aante Onkoleessa 22 nna 23 hossannoti Ficheenkeeti. Konni ayyaanira diinu adawanke hunara qodhe ka’annoha ikkara dandaannota ejjeetto seekkite huwattanno. Kuni Ficheete ayyaani keerunni sa”anno gede baalunku qarqarira noo ejjeetto ayyaana beeqqanno mannira adawu hajo lainohunni huwanyo kalaqqanno gede sokka sayissanno.

Saeno, woraddanna quchummatenni ayyaana ayirrisara Hawaasa daanno manni ledo dagge, dagansanna quchuminsa adawa agadhitanno gara woradunna quchummate gashshooti ledo malantanno gede ejjeetto qaagiissitanno.

Sidaamq, aye gedeno ikkite Fichee qara sirnyanke balaxxe daggurono, baalunku Sidaami illachasi QOQQOWU hajo aana wora hasiissannotanna diinu abbe wixanno biilloontu, woxu, horonna wkl manaadurichinni deama hasiissannosikkita ejjeetto seekkite qaagiissitanno.

Tini Sidaamu Wolaphora Sharrantanno Goofimarchu Ilamaati!

Qeelleemmo!

Ejjeetto
Hawaasa, Sidaama| ETHIOPIA

በወቅታዊ የትግል ሁኔታዎች ላይ የሲዳማ ኤጄቶ ያወጣው የአቋም መግለጫ

በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ የሲዳማ ኤጄቶ በሀዋሳ ከተማ ባህል ማዕከል አዳራሽ በአጠቃላይ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በተለይም በሲዳማ ህዝብ የክልል ጥያቄ፣ በፀጥታ ጉዳዮች ላይ እና በቀጣይ የትግል አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ያደረገ ሲሆን ከዚህ በታች የተገለፀውን የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
“በወቅታዊ የትግል ሁኔታዎች ላይ የሲዳማ ኤጄቶ ያወጣው የአቋም መግለጫ”
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
“ለሲዳማ የክልልነት ጥያቄ የሚታገል የመጨረሻው ትውልድ” በሚል መሪ ቃል ህጋዊና ሰላማዊ ትግል እያደረገ የሚገኘው መላው የሲዳማ ህዝብ ወይንም ኤጄቶ ከምን ጊዜውም በላይ አንድነቱን አጠናክሮ የትግሉን ፍሬ ለመሰብሰብ የቀረው እጅግ ጥቂት ጊዜ መሆኑ ይታወቃል።

ይህንን ሰላማዊ ትግል ይዘቱን ለመቀየር የተለያዩ ፖለቲካዊ ሴራዎች የተሞከሩ ቢሆንም ፅኑ አቋም በያዘውና የሲዳማ አንድነት ላይ በማይደራደረው ኤጄቶ ትግሉ አሁን የደረሰበት ደርሷል።

በመሆኑም ይህንን ትግል ከዳር ለማድረስ በምንተጋበት በዚህ ጊዜ ጠላት የተለያዩ የተስፋ መቁረጥ ሴራ ሙከራዎች በደኢህዴንና ተላላኪዎቻቸው እየተሞከረ መሆኑን ደርሰንበታል።
ስለሆነም የሲዳማ ኤጄቶ ትግሉን ለማስቀጠል የሚከተሉትን የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

1. ኤጄቶ የሲዳማን ህዝብ የዘመናት ጥያቄ ለአንዴና መጨረሻ ጊዜ እንዲመለስ ከየትኛውም ፀረ-ህዝብና ጨቋኝ አስተሳሰብ አራማጅ ኃይሎች ጋር እልህ አስጨራሽ ሰላማዊና ህገመንግስታዊ ትግል የሚያደርግ የመጨረሻው ትውልድ አካል እንጂ የመንግስት ወይንም የፓርቲ ጉዳዮች አስፈፃሚ ቡድን አይደለም።

ስለሆነም በስመ-ኤጄቶ ፀረ-ትግል ተልዕኮ በመውሰድ የህዝባችንን የዘመናት ትግል ዋጋ በማሳጣት ወደነበረበት ዘመናዊ የባርነት ዘመን ለመመለስ በሲዳማ ምድር የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችንም ሆነ ቡድኖች አጥብቀን የምንቃወም ሲሆን አስፈላጊውን ሁሉ በማድረግ ከተግባራቸው የምናስቆማቸው መሆኑን እናሳውቃለን።

ህብረተሰቡም እኩይ ተልዕኮ ከበስተጀርባ ይዘው ጠቃሚ የሚመስሉ በማር የተለወሱ መርዞች ሲቀርቡለት በተለመደ የማስተዋል ጥበቡ ለይቶ እንዲያወጣና እንዲያጋልጥ እንጠይቃለን።

2. ኤጄቶ ማለት በራሱ ለህዝብ ሁለንተናዊ ነፃነት በትጋት፣ በፅናትና በቁርጠኝነት ህግን ተከትሎ የሚገባውን የሚጠይቅና ለብዙሃን ጥቅም የራሱን ህይወት አሳልፎ እስከመስጠት የሚታገል እውነት ላይ የቆመ የህሊናው ባሪያ ማለት ነው።

ለግል ጥቅማጥቅም፣ ሀብትና ስልጣን የሚሮጥ፣ የራሱን ሰብዓዊና ህገመንግስታዊ መብት ለማስከበር የሌላውን የሚደፈጥጥ፣ ከመርህና እውነት ይልቅ በጊዜያዊና ግላዊ አጀንዳ ላይ ውድ ጊዜውን የሚያጠፋ ከንቱ ትውልድ አይደለም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚህ የትግል እንቅስቃሴ መሰረታዊ መርሁን ጠብቆ የህዝባችንን የዘመናት ትግል አሁን የደረሰበት ደረጃ ፍፁም ህጋዊ በሆነ መንገድ ለማምጣቱ መላው ዓለም ምስክር መሆኑ እየታወቀ ትግሉን ለማቀዝቀዝና የኤጄቶን ህልውና ለመፈታተን ኤጄቶን እንደሽፋን በመጠቀም ተራ የስርቆት ወንጀል የሚፈፅሙ ጥቂት ወጣቶችን መንግስት ሆን ብሎ እያየ እንዳላየ በመሆን ወንጀለኞችን እያበረታታ እንደሆነ ደርሰንበታል።

ስለሆነም በመላው ሲዳማ ምድር መንግስት በወንጀለኞች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ እያሳሰብን ሂደቱን በከፍተኛ ጥንቃቄ የምንከታተለው መሆኑን እናሳውቃለን። ይህ ካልሆነ ግን መንግስት ህግ ለማስከበር አቅም እንዳጣ በመቁጠር ኤጄቶ የመላው ሲዳማንና ሌሎች ነዋሪ ወንድም ዜጎች ደህንነት ለመጠበቅ የሚሰራ መሆኑን እናሳውቃለን።

3. ደጋግመን “ይህ ትውልድ ለሲዳማ ክልል ጥያቄ የሚታገል የመጨረሻው ትውልድ ነው” ስንል ከምራችን ነው።
ስለሆነም ላለፉት 8 ወራት ከህፃን እስከ አዋቂ፣ ከሴት እስከ ወንድ፣ ከአርሶአደር እስከ ምሁር አለምን ያስደመመ ሰላማዊ የትግል እንቅስቃሴ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ የቆየ መንግስት ሲዳማ ምላሹን ሳያገኝ ህገመንግስታዊ የጊዜ ገደብ ከተጠናቀቀ በራሱ ክልል ለማወጅ በሚዘጋጅበት በዚህ ባለቀ ጊዜ ለውይይት መጋበዝ ትግሉን ከማዘናጋትና ከማጨናገፍ የዘለለ ፋይዳ እንደማይኖረው ኤጄቶ በፅኑ ያምናል።
ባይሆን መንግስት ኢ-ፍትሃዊ የሆነውን ደቡብ የሚባለውን አደረጃጀት በማፍረስና በሀገሪቱ የፌደራሊዝም ስርዓት መልሶ በማደራጀት የቆዩ ህዝባዊ ጥያቄዎችን ቢመልስና ዘላቂ ሰላም ቢያሰፍን እንዲሁም የሪፎርሙ ዋና አካል በማድረግ ሪፎርሙን እውነተኛ እንዲያደርገው እንመክራለን።
ውይይት ማድረግ አለማድረግ የሚሉ የሀሳብ ልዮነቶችን የዓላማ ልዩነት በማስመሰል ህዝባችንን ለመከፋፈል የሚደረግ ማንኛውንም እንቅስቃሴ የምንቃወም መሆኑን እየገለፅን ገፍተው ትግሉን አደጋ ላይ ለመጣል የሚሯሯጡ ጥቂት ግለሰቦችን ግን የማንታገስ መሆኑን እንገልፃለን።

4. ቀጣይ የትግል አቅጣጫዎች ሁለት መጠቅለያ ላይ የተንጠለጠሉ መሆናቸው ግልፅ ነው። በተጀመረው ህገመንግስታዊ ሂደትን የተከተለ ሪፈረንደም አካሂዶ ውጤቱን ለህዝቡ ማሳወቅ ወይንም ደግሞ ህገመንግስታዊው የጊዜ ገደብ ሲጠናቀቅ የራስ አስተዳደር ክልል በማወጅ የፌደራል መንግሥቱን መቀላቀል ናቸው።
ሁለቱም የራሳቸውን ዝግጅት የሚፈልጉ ቢሆንም የሚቀድመውን እያስቀደምን ለሁለቱም የምናደርገውን ዝግጅት አፋጥነን የምንገፋ ሲሆን ለዚህም
ሀ. ህገመንግስታዊ የማስፈፀም ስልጣን የተሰጠው የክልሉ ም/ቤት እንዲሁም የመፈፀም ግዴታ ያለበት ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ቀሪ ጊዜውን በአግባቡ በመጠቀም ተግባራቸውን ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ እንዲፈፅሙ አጥብቀን እንጠይቃለን።
ይህ ካልተፈፀመ ጋዶ 4 በቅርብ ጊዜ የምናውጅ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።
ለ. በሌላ በኩል ክልልን ህገመንግስታዊ በሆነ መንገድ ለማወጅ ዝግጅት እንዲያደርግ ኃላፊነት የተሰጠው የክልል ዝግጅት ሴክሬታሪያት የደረሰበትን ለህዝብ በተከታታይ በማሳወቅ በየደረጃው ህዝባዊ ውይይቶች በአስቸኳይ መጀመር እንዳለበት አጥብቀን እንጠይቃለን።

ሚያዝያ 23/2011 ዓ.ም
ኤጄቶ
ሀዋሳ ሲዳማ ኢትዮጵያ

Sidaamu Hajo Aana Ejjeettote Uurrinsha Xawishsha 

HASAAWA AGURINA HANUKKI DIYINEEMMO!

Riferaandemete barra mure kullanke geeshsha ayeeno diawuutinseemmo!

Sidaamu wolaphate xa’mo xa’me anfanni rarraanseenna koffeenyasi kula hanafinku aganna kiirantino. Afuu geeshshira Xa’monke jawiidi Seera agadhitinote yinanninke ikkinnina Seeru yaanno harinsho gumulle Seera diayiirrinsoonni. Agarre hoongoommo.

Jawiidi Seera(Higge mangiste) ayiirrisse loossanno yine agadhinanni xaano galaalchinannilla hee’noommo.

Yaadigi Songora Xa’mo’ne “Higgemangittaawete, ayiino badhera diqolanno” yinoyiinke! Yaateno gadadu noonsa. Mule assini songorano hattennella lendoonni. Baxxinori lowori dino.

Onkoleessu 15/2011 M.D kawa Wodiidi diigame sasewa woyi shoolewa beehamannotano hare higi manni kayiisanno. Sidaamu xa’mono hojja amadante Riferaandemetenni goofate injiitannota hasaabbino. Seeru harinshono ikka hoogiro.

Riferaandemete barra murroonniyya? Dimurroonni! Mayiira? Hare higi manni dixawisino!

Hare higi manni maa adhe higixa?

Dr. Abiyyi Sidaamu manna hasaawara hasirinotanna manna doorre soyaate! Maaho hasaawisaraati? Danfoonni. Riferaandeme keeshshiisha, Laga Daarra widi daga ledo xalla, xa’monke huna, Rodiimmate xaado ledo, keereho halama…w.k.l aantetenni ikkara dandaanno.

Ejjeetto mayyiituyya??

👉Riferaandemete barra murrikkinni assinanni hasaawa tiyyidhe gibbino!

👉Shawwa hadhe hasaawateno horonta dihasidhanno.

👉Onkoleessa 15/2011 M.D albaanni assinanni hasaawano dihaadhanno.

Hasaawa hasirino manchi qae mare xa’mira noositanna yakka yakkisino meentu ejjeettora dawaro qollikkinni wole doogonni hara budenke dikkino!

Konni daafira

Sidaama ikkinohunna Sidaamu wolapho hasirannohu Hasaawaho yaanni hembeelama dinosi.

Hasaawiseemmo yaannohuno tenne wodho gumulikkinni wo’naalara didandaanno!

Higge mangittete wodho mitte hinge hiiqqiniro, cancantara doogo murte fultino horophillaati!”…Balaxinore tunge, dayiinorira dodama baalanka daafursitanno.

Ayeeno ikko maa, Onkoleessa 15 albaanninna Riferaandemenke barri murame kulamikkinni giwe hasaaweemmo yaannohu Sidaama hirannoho. Baarigaarankeeti.

👉Hasaawiseemmo yaannohuno heeriro deerra deerraho noo ejjeetto qaafo adhate gadadammeemmo!

Aleenni wodhinummo hajo gooffuronna taalturo dagoomaho iillishi’neemmota anfe mulinkenni woy qarqarinkenni milli yitanno lekka agarro!

Tini ilama ayee ganyano dikkitino!

Tenne ilama hasatto, Sidaama wolassate Sharrantanno goofimarchu ilamaati!

Ejjeetto

16/08/2011
Hawaasa,

Sidaama

ETHIOPIA

ከሲዳማ ጥያቄ ጋር ተያይዞ ለሚደረግ የትኛውም አይነት ድርደር ከሲድማ ኤጄቶች የተሰጠ የአቋም መግለጫ!

የሲዳማ ህዝብ የራሱን ክልል መስርቶ ራሱን በራሱ ለማስተዳደር ከፍተኛ የሆነ የህይወትና የአካል መስዋእትነት ሲከፍል መቆየቱ ይታወቃል።

በዚህ ሂደት በተለያዩ ግዜያት የሲዳማ ህዝብ መብቱን ለማስከበርና ህገ መንግስቱ ገቢራዊ እንዲሆን የሚጠበቅበትን ህገ መንግስታዊ ሂደቶችን ጨርሶ ወሳኝ ደረጃ ከደረሰ በኋላ አላስፈላጊ መደለያዎችንና መደራደሪያዎችን በማቅረብ እንዲሁም ታጋዮችን ነጥሎ በመምታትና በማሸማቀቅ ጥያቄያችንን ለመቀልበስ አደገኛ ፖለቲካዊ ሴራ ሲዘራ እንደነበር ይታወሳል።

አሁን የሲዳማ ህዝብ ጥያቄ የደረሰበት ደረጃና ግዜ ለህጋዊ ጥያቄ ህጋዊ ምላሽ የሚፈልግ እንጂ ድርድር የሚደረግበት አይደለም።

ይሁን እንኳን ቢባል እስከ ዛሬ ኤጄቶ ስያንጸባርቅ ለነበረው ሰላማዊ ተጋድሎ ጆሮ ሳይሰጥ የቆየው የፌደራል መንግስት ዛሬ የራሳችንን ክልል በራሳችን ለማወጅ ቅድመ ዝግጅት እያደረግን ባለንበት ዋዜማ ህዝባችንን ጥርጣሬ ውስጥ ሊያስገባ የሚችል ከፋፋይ ደኢህዴናዊ አጀንዳ በማምጣት ጥያቄያችንን ለመቀልበስ አልያም ጋብ እንዲል የሚደረጉ ርብርቦች መርህ የለሽ እንቅስቃሴዎች ከመሆናቸውም ባለፈ በትግላችን ላይ ምንም አይነት ተጽእኖ የሚፈጥሩ አለመሆናቸው ግልጽ ነው።

በዚህም መነሻነት የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ቀን ተቆርጦ ለህዝባችን ይፋ እስኪደረግ ከየትኛውም የፌድራል አመራር ጋር ምንም አይነት ድርድር እና ውይይት ለማድረግ ፍቃደኛ አለመሆናችንን አጥብቀን እናሳውቃለን።

ይህ በእንዲህ እናዳለ ህገ መንግስቱ ህዝበ ውሳኔ ለማደራጀት ለክልሉ ም/ቤት የሰጠው ቀነ ገደብ 85 ቀን ብቻ የቀረው ሲሆን በነዚህ ቀሪ ቀናት ውስጥ የሪፈረንደም ቀን ተቆርጦ ወደ ህዝበ ውሳኔ የማይገባ ከሆነ የሲዳማ ዞን ም/ቤት የሲዳማን ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት እንዲያጸድቅ አስፈላጊውን ጫና ሁሉ ለመፍጠር የምንቀሳቀስ መሆኑን አጥብቀን እናሳውቃለን።

ሲዳማ

ኤጄቶ

ሃዋሳ

16/08/2011