የሲዳማ ኤጄቶ ዛሬ መጋቢት 19/2011 ዓ.ም ካደረገው አጠቃላይ ስብሰባ ያወጣው መግለጫ ሙሉ ቃል

#የሲዳማ ብሄር በክልል የመደራጀት ጥያቄ በዞኑ ም/ቤት በሙሉ ድምጽ ጽድቆ በህገ መንግስቱ መሰረት በደብዳቤ መልክ ወደ ደቡብ ክልል ም/ቤት ተልኮ ተቀባይነት በማግኘቱ ለህዝበ ውሳኔ አፈጻጸም ወደ ም/ቦርድ መላኩ ይታወሳል። ይህ ከሆነ ወራቶች ተቆጥረዋል። እስከ ዛሬ ድረስ ቦርዱ አንዳች ህገ መግስትስዊ ምላሽ ለህዝባችን ጥያቄ አለመስጠቱ የቦርዱን፡ገለልተኛነት በጥርጣሬ፡ውስጥ እያስገባ ከመሆኑ ባሻገር የህዝቦች ጥያቄ ህገ መንግስታዊ በሆነ መልኩ ምላሽ እንዲያገኝ የሚያስችል ፖለቲካዊ ለውጥ አድርጌያለው እያለ ያለው መንግስት ከህዝባችን ጥያቄ ጎን ከመሰለፍ ይልቅ የህዝበ ውሳኔው ግዜ ኢ ህገ መንግስታዊ እና ጸረ ዴሞክራሲያዊ በሆኑ ተራ ምክንያቶች ይፋ እንዳይደረግ ጥረቶችን እያደረገ ይገኛል።

በዚህ ምክንያት የሲዳማ ኤጄቶ የተለያዩ ሀገር በቀል የትግል ፡ስልቶችን ታክቲኮችን በመጠቀም የህዝብ ድምጽ እንዲሰማ፡ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። እስካሁን ድረስ ሀገርን ያስደመሙ ሁለት ታላላቅ ጋዶችን የፈጸምን ሲሆን በዚህም የህዝባችንን ድምጽ በበቂ መልኩ ማሰማት ተችሏል። ያም ሆነ የሚመለከተው አካል አሁንም ለህዝባችን ጩኽት ጆሮ ባለ መስጠት ጥያቄያችንን ችላ ማለቱን እያሳበቀ ይገኛል።

በመሆኑምይ የሪፈረንደም ቀን ሳይገለጽ በዚህ መልኩ በቆየ ቁጥር በሀገር ደረጃም ይሁን በአከባቢያችን ሊፈጥር የሚችለው፡ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ቀውስ አደገኛ በመሆኑ መንግስት አስቸኳ ምላሽ እንዲሰጥ እንጠይቃለን። መንግስትም ይሁን ምርጫ ቦርዱ በንዲህ ያለ ቸልተኝነት የሚቀጥል ከሆነ ኤጄቶ በቅርቡ 3ኛውን ጋዶ ለማወጅ ዝግጅቱን እንደጨረሰ ለማሳወቅ እንወዳለን።
ይህ በንዲህ እንዳለ ላለፉት በርካታ አመታት የህዝባችንን ሀብት ምክንያታዊ ባልሆነ መልኩ እየዘረፈ በግዞት ያቆየን ደኢህዴን በቅርቡ በህዝባችን ባጠው ቅቡልነት የተነሳ ከሲዳማ ምድር ህላዊ እንዳይሆን መደረጉ ይታወሳል።

ይህ እንዲሆን የተደረገው ድርጅቱ ከህገ መንግስቱ መርህ ውጪ የሆነ አማራጭ በመያዝ ህዝባችንን ለማወክ ከያዘው ግትር አቋም መነሻነት እንደሆነ ግልጽ ነው። ይህ ሆኖ ሳለ ድርጅቱ እንደ ገና አፈር በመቃም ለመንሰራራት የቀደመውን የሴራ መረብ ለመዘርጋት ደፋ ቀና እያለ ይገኛል።

ለዚህ ተልእኮው ይረዳው ዘንድ ቀድሞ ይደረግ እንደነበረው ሁሉ የመ/ሰራተኞችን ደመወዝ ያለ ሰራተኞቹ ፍቃድ በመቁረጥ አላስፈላጊና ወቅቱን ያልጠበቀ ሹም ሽር በማድረግና በአመራሮች መሀከል ያለውን መተማመን እና አንድነት ሊሸረሽር የሚችል ብወዛ በመተግበር የትግላችንን አቅጣጫ ለማሳት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን መረዳት ችለናል። በመሆኑም ከዚህ በኋላ የዚህን ድርጅት አላማና ተልእኮ በማንገብ የሚደረግ የትኛውም፡አይነት እንቅስቃሴ ጸረ ሲዳማ መሆኑ ታሳቢ የሚደረግ ሲሆን ኤጄቶ ይህን አጀንዳ ይዘው በሚነሳቀሱ ሀይሎች ላይ ተመጣጣኝ እርምጃ እንደሚወስድ፡ልናሳውቅ እንፈልጋለን።

#ይህ በንዲህ እንዳለ ጥቂት አውደልዳይ እና ጥቅመኛ ባንዳዎችን በመቅጠር ትናንሽ አጀንዳዎችን በህዝባችን ላይ በመጫን ከዋናው የትግል አላማችን ለማንሸራተትና ህዝባችንን ከፋፍሎ የትግል፡አቅማችንን የሚፈታተኑ ሀይሎችን ከዚህ በኋላ የማንታገስ ከመሆኑ ባሻገር ጉዳዩን አምርረን የምንታገል መሆኑን ለሚመለከተው አካል ሁሉ ማሳወቅ፡እንወዳለን።

19/07/2011 ዓ/ም

ሀዋሳ

 

Ejjeettote Uurrinsha!

Techo Badheessa 17, 2011M.D Ejjeetto Wiinamu Songo Songite, Lamu Sirinyi Aana Aane Nooha Uurrinshate Xawishsha Fushshitino!

1.Layinki gaadi albaanni Deedeni Sidaamu xa’mo gufisate qixxeessino sanade kaiminni aanasi kaajjado qaafo adhinoonniti qaangannite. Konni korinni, Deedeni Sidaamu Zoonenna Hawaasi Quchumi Gashshooti giddo wolqa afi’rannokkiha assine keeshshinonni.

Xaa yannara Deedeni mereerima komite miilla ikkitinori Sidaamu xa’mo aana huluullo kalaqate untanni noo bale suunfe iillinoonni.

Konnira, Sidaamu xa’mo jeefo gansiisate Deedeni buqqisantenni roore, hee’re reyanno qaafo adha hasiissino.

Hee’re reyanno gede assate qara hayyo, miilla aganunni baaxxitanno fushsho ittisanna Deedenita aye songono songa agura hasiissannota hasaambe sumuu yinoommo.

Ikkinohurano, konni aganinni kayinse, Sidaamu Zoonenna Hawaasi Quchumi Deedeni Miilla Aganu Fushsho (መዋጮ) baattannokki gede kaajjinshe sokka sayinsanni qoleno, Deedeni su’minni aye songono songa hasiissannokkita duu’ne xawinseemmo. Ledeno, konni sirnyi gumulo albankeenni Hamusete barra heedhannonke xaphoomu songonni dhaambeemmota ikkitanno.

2. Deedenino ikko ali gashshooti Sidaamu xa’mo injiisaro duumba qolate, woy xiinxallotenni dawarate, hakkiinni sa’uro, keeshshiishate hasatto noonsata ordinsa leellishanno. Tenne mixonsa gafa gansiisate horonsidhanno hayyo giddonni mitte ninke ninkewa mimmito huluullammeemmo ajanda kalaqa ikkinota keennoommo.

Hattenne hexxonsa gafa gansiissate tafa tuqqino garinni anfeno ikko afa hoogatennk yannara meessi manni sada addi addi doogonni feesibuukete aana kayinsanni keeshshinooniti mittimmanke jifate deerra iillitinota masaalloonni.

Konni ka’a kayinni, giddoydi hajo lammeessine, Sidaamu Xa’mo aana calla illachisha hasiissino. Ikkollana, polotiku qiniite adhate amaalamme giddo baandooti aana mitteenni adhinara qaafo agurranna techo barrinni kayinse, meessi manna feesibuukete aana suntannikki gede duu’ne sokka sayinsanni, jaddote korkaatinni coyinsa higgete anga noo mannooti hajo meessa hi’ra e’nikkinni higgete garinni gumulo afidhanno gede xawinsanni, higgete aana hekko kalaqatenni daga hembeelsitanno mannooti eemadhitanno gede egensiinseemmo.

Tini Ilama Sidaamu Qoqqowo Xintate Sharrantanno Goofimarchu Ilamaati!!

Ejjeetto
Hawaasa,

Sidaama

Ethiopia

ከኤጄቶ እውቅና ያገኘ ሰልፍም ይሁን የስራ ማቆም አድማ ነገ በሀዋሳ የለም:: ከሀሰተኞች ተጠበቁ!

ግርግር ለሌባ ይመቻል እንዲሉ ከሰሞኑ የኤጄቶን ስም ለማጥፋት ቆርጠው የተነሱ አካላት በሀዋሳ ከተማ የሀሰት መረጃ በማሰራጨት ህዝቡን ለማሸበር እየጣሩ ይገኛሉ። ኤጄቶ ሰልፍም ይሁን የስራ ማቆም አድማ ሲያውጅ በአሉባልታ ሳይሆን ከሽማግሌ ተማክሮ በአንድነት ተነጋግሮ ግራ ቀኙን አይቶ ነው። ሰሞኑን ከሲዳማ ውስጥም ሆነው ከውጪ ሀይል ጋር በማበር የኤጄቶን ስም ለማጥፋት እየተንቀሳቀሱ ነው። ስለዚህ መላው የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ በዚህ የሀሰት መረጃ ሳይሸበረ ወደ መደበኛ ስራው እንዲሰማራ እመክራለው።

ሊሰመርበት የሚገባው ጉዳይ “ጥያቄያችን ሕገመንግሥታዊ፣ ትግላችን ሠላማዊ” መሆኑን ሁሉም ዜጋ በመረዳት ለአከባቢው ሰላም ዜብ መቆም አለበት እንላለን:

የጋዶ 2 ስራ ማቆም አድማ መጠናቀቁን አስመልክቶ ከኤጄቶ የተሰጠ የምስጋና መግለጫ!

ባለፉት ሶስት ቀናት የሥራ ማቆም አድማ በሲዳማ ኤጄቶ ታውጆ እንደነበር ይታወሳል። አድማውም በሁሉም ሲዳማ ወረዳዎች በተሳካ ሁኔታ ተደርጓል።

አንዳንድ ፀረ-ህዝብ ተቋማትና ድርጅቶች አድማውን ለማስተጓጎል ቢሞክሩም። ወጣም ወረደ አድማው ትናንት ማምሻውን ተጠናቋል።

አድማው (Gaado 2) ላይ እንደበፊቱ እግዚአብሔርም ምስክርነቱን በመስጠት በሰላማዊው ሰልፍ ማጠናቀቂያ ላይ ዝናብ ሰጠ። ዛሬም ሲዳማ ላይ ዝናብ በመዝነብ የእውነት አድማ መሆኑን ፈጣሪ ምስክርነቱን፣ ሽማግለዎቹም ምርቃታቸውን ሰጥተው አረጋግጠዋል። ፈጣሪም ቸር ፈራጅ ነውና ምስጋና የሚገባው ነው! ለዚህ የፍትህ ትግል ሰላምም ምስጋና ይገባዋል።
….
“የሲዳማ የረፈረንደም መቆየት የኔም ጉዳይ ነው” በማለት አብሮን የተሰለፉ ድርጅቶችና ተቋማትን እንደኤጄቶ ማመስገን ግድ ይለናል።

በመጀመሪያ ሰላማዊ ትግሉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጉልበቱን አማጦ የተጠቀመው የነጻነት ጮራ ለሆነው ኤጄቶ አባላትና ሲዳማ ህዝብ ምስጋና አቅርበናል።

በመቀጠልም በሲዳማ ምድር በኑሮም ሆነ በንግድ የተሰማሩ ወንድም ህዝቦችን ማመስገን እንፈልጋለን። በተለይ ትኩሳቱ ማዕከል ለሚኖሩ ለሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች።

ሌሎች የመንግስት ተቋማትና ሠራተኞችን፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችንና ሰራተኞችን እንዲሁም ተማሪዎችና መምህራንን ማመስገን እንፈልጋለን።

የሲዳማ ዲያስፖራ ማህበረሰብም እንደወትሮው ላደረጉት የሰለጠነ እንቅስቃሴ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው።

በግል ማህበሣዊ ገጻቸውም ሳይቀር ለተከታዮቻቸው የአድማውን ዓላማና ቀጣይ ውጤት አስመልክቶ ለሰጡት መግለጫ ወንድም ቄሮንና በተለየ ሁኔታ የኦሮሞ አክቲቭስቶችን በዋናነትም አቶ ጃዋር ሞሐመድን ከልብ እናመሰግናለን።

የደኢህዴን ባርነት አንገሽግሾአቸው የሲዳማን መናቅና መረገጥ ፊለፊት በመቃወም የደኢህደንን ልብ የሰበሩትን የወረዳዎችና የመምሪያዎች ካድሬ አባላትን ሳናመሰግናቸው አናልፍም። ምንም እነሱም የጋዶ አባላት ቢሆኑም።

በሲዳማ ውስጥ የሚፎካከሩና ሀገር በቀል የሆኑ ፓርትዎችም ከህዝብ ድምጽና ቅሬታ ጋር በመሆናቸው ኩራት ተሰምቶናል።

የሥራ ማቆም አድማውንም ባልተበረዘና በተገለጸው ልክ ለኢትዮጵያ ህዝብና ደጋፊዎቻችን የቀጥታ ሽፋን ለሰጡ ሚዲያ ተቋማት ምስጋናችን የላቀ ነው። በተለይ OMN ውለታው የሚረሳ አይደለም። EBC, FANA, WALTA፣ OBS እና ሲዳማ ቲቪን እንድሁም ለዓለም ህዝብ ያሰማው BBC እናመሰግናለን።

በመጨረሻም የህብረተሰቡ ደህንነት እንዲጠበቅ የበኩላቸውን የተወጡትን በአድማው ክልል ወሰን የነበሩ ፖሊስ አካላትንና ግለሰቦችን ማመስገን ይፈልጋል።

በተቃራኒው ደግሞ ስራ ለመዝጋት የተገራገሩና ኋላም ለመዝጋት የሞከሩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀዋሳ ዋናው መስራየ ቤትና ሁለት ቅርንጫፎቹ ናቸው።

የሀዋሳ ኢንዲስትሪ ፓርክ የተወሰኑ ብሎኮችም ለአብነት ሼድ 17 የመሰሳሰሉት ከአሰሪ ከአቶ አንዱዓለም አለባቸውን ጨምሮ ሥራ ለመስራት ጥረዋል።

ጸረ-ህዝብነቱን በማመሳከር እየቀጠለ ያለው ኢሳት ቴሌቪዥን አድማውን ሚዛናዊነቱን በማጣመምና በስድብ ዘግቧል። የኢሳት ጋዘጤኞች ሀዋሳ ከተማ እንዳይገቡ በመከለከላቸውም ለብቀላ የሰሩት ዘመቻ እንደሆነም ኤጄቶ ያምናል።

ሙሉ በሙሉ ደግሞ ደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት አለመዝጋቱን አረጋግጠናል። በፈደራልና ልዩ ኃይል መከታም መተመተማመኑን ተመልክቷል። በእርግጥም በጋዶ 2 ምንም እርምጃ ለመውሰድ አቋም ስላልነበረ መረጃ ተይዞ ታልፎለታል። ይህ ደግሞ በጣቢያው የሚጠቀመውን የሲዳማ ቴሌቪዥን አይመለከትም እሱና ሰራተኞቹ ዘግተው ውሎአልና።

ምንም ያህል የክልል መስሪያ ቤት ቢሆንም የደ/ብ/ብ/ህ/ክልላዊ መንግስት ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የአበል እጥረት ስላጋጠመው አድማውን መቀላቀል አልፈለገም።

የሙት መንፈስ የሆነው የአንዳንድ የፈዴራል ፖሊስና የፈራሹ ክልል ልዩ ሀይል በሰላማዊ ቤተሰብ ላይ በወሰዱት እርምጃም በሰው አካል ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ማድረስ ችለዋል። የዚህ ሱስ ቀጣይ አካል የሆነውም የአድማውን ቀን ለማሳጠር በደቡብ ቴሌቪዥን ቀርቦ የሰጡት የማስፈራራየ መግለጫ የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ እምነት በማጣቱ ሳይሳካላቸው አድማው ቀጥሎ በተባለው መንገድ ተጠናቋል።

ገጠር ወረዳዎች ላይ ግን የሚሰማቸው እንኳን አልነበረም አይኖርምም። ከነዚህ መግለጫ ሰጪዎችም ውስጥ ተገድደው መግለጫ የሰጡም እንዳሉ አረጋግጠን Bado ብለን አልፈናል።

ለዚህ ሁሉ የረፈረንደም ቀን ተቆርጦ የማይነገር ከሆነ ሰላማዊ እርምጃ ልወሰድ እንደሚወሰድ
ግንዛቤ ውስጥ ይገባል። ለባንኩ ተጠቃሚን ሌላ ባንክ አማራጭ ማስቀየስ ያስተምራቸዋል። ሌላውንም አስተማሪና የተጠና የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ ኤጄቶ አቅምም እውቀትም አለው።

የሚመለከተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤትና የደ/ብ/ብ/ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ጉዳዪን አስመልክቶ ምንም ያሉት ነገር ባይኖርና ሰላማዊ ግፍቱ ራስ ምክር ቤቶች እስከመወሰን ድረስ ይቀጥላል።

ይህ ሁሉ ሆኖ ግን የረፈረንደም ቀን ተወስኖ ለሲዳማ ህዝብ ይፋ የማደረግ ከሆነ የጠለቀና አስከፊ ሰላማዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ከወዲሁ ይመዘገብልን።

ጋዶ 3 በቅርብ እንዲታወጅ #የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት እየገፋፋን መሆኑንም ልብ ብላችሁ ጋዶው እንዲቋረጥ ቀኑ እንዲገለጥ የድርሻችሁን እንድትወጡ ኤጄቶ ጥሪውን ያቀርባል።

“ይህ ትውልድ ለሲዳማ ነጻነት የሚታገል የመጨረሻው ትውልድ ነው” ኤጄቶ

ኤጄቶ

ሀዋሳ፣ ሲዳማ፣ ኢትዮጵያ
መጋብት 7/2011 ዓ.ም

የ2ተኛ ዙር ጋዶን በሰላም መጠናቀቅ አስመልክቶ ከኤጄቶ የተላለፈ መልእክትና ምስጋና

የሲዳማን ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄን ተከትሎ ጥይቄው ህጋዊ መንገዱን ጠብቆ በመሄድ ላይ ይገኛል። በመሆኑም በተለያዩ ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነቶች እየተስተጓጎለና እየተጓተተ መሆኑን ተከትሎ የሲዳማ ኤጄቶ ሰላማዊ የትግል አዋጅ (ጋዶ) በማወጅ በጋዶ #1 በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ የተሳተፈበት በሀዋሳ ከተማ የተካሄደ ፍፁም ሰላማዊ የሆነ ሰልፍ በየካቲት 14/2011 መደረጉ ይታወሳል።

በዚህም የኢትዮጵያ መንግስት ለህዝቡ ምላሽ ሳይሰጥ በመቆየቱ ጋዶ #2 መታወጁ ይታወቃል፡፡ በዚህም የተመረጡ ተቋማትን የስራ ማቆም አድማ ከመጋቢት 4-6/2011 ጥሪ ተደርጎ እንደነበር ይታወቃል።ጥሪውን ተከትሎ በመላው የሲዳማ ምድር የተሳካ አድማ ተደርጓል። ለዚህም መሳካት መላው የሀዋሳ ከተማ እና ሲዳማ ዞን ህዝብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል።

ላለፉት በርካታ አመታት ደኢህዴን ህይወት እንዲኖረው የተደረገው በዋናነት በሲዳማ ህዝብ ላይ ጠላት በማብዛትና ሊሎች ብሄሮች በህዝባችን ጥያቄ ላይ ጥርጣሬ እንዲኖራቸው በማድረግ እንደነበር ይታወቃል። ይህ በጠላት ጠንሳሽነት የተንሸዋረረ ምልከታ ሙሉ በሙሉ እንደማይሰራ በሀዋሳ ከተማ የሚኖሩ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች ከሲዳማ ህዝብ ጥያቄ ጋር በመሰለፍ ለሲዳማ ህዝብ ጠላቶች ግልጽ መልእክት አስተላልፈዋል።

ምስጋና

ጥያቄያችሁ ጥያቄያችን ነው ብላችሁ ሀዋሳን ጨምሮ በሲዳማ ወረዳ ከተሞች የምትገኙ ነዋሪዎች፣ ባንኮች፣ የመንግስት መ/ቤቶች፣ ከፍተኛ የት/ት ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ኢንዱስትሪ ፓርክ ሠራተኞች በሙሉ፤ ምስጋናችሁ የሲዳማ ነፃነት ይሁን።

መልእክት

የሪፈረረንደም ቀን በቅርብ ተቆርጦ የማይነገር ከሆነ ይህ ሰላማዊ ትግል በቀጣይነት በመጠን እና በይዘት ሰፋ ባለ መልኩ ተቀጣጥሎ ይቀጥላል። ይህን ትግል ለመቀልበስና የትግሉን አቅጣጫ በማሳት የሲዳማን ህዝብ ትግል አጠልሽታችሁ ለመቀልበስ የታተራችሁ ሀይሎች ዛሬም በኤጄቶ ትጋትና በሲዳማ ህዝብ አጋሮች ጥረት ድባቅ ተመትችኋል። ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ጋዶ#3 እስኪታወጅ ድረስ መላው ሲዳማ ወደ ቀድሞ እንቅስቃሴ የሚመለስ ይሆናል።

የጋዶ #3 ዝግጅትም የተጠናቀቀ መሆኑን በአፅንኦት እናስገነዝባለን!!

ኤጄቶ
መጋቢት 6/2011 ዓ.ም
ሀዋሳ ሲዳማ ኢትዮጵያ

በኤጀቶ የተጠራዉ የሥራ ማቆም አድማ ረቡዕ፣ ሀሙስና ዓርብ(4-6/7/11ዓም) የከናወናል

የሲዳማ ብሔር ራስን በራስ ለማስተዳደር ካለው ጽኑ እምነት ብዙ ዋጋ ከፍሎአል። ህገ-መንግስት ተከብሮ ለማየትም የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ሰላማዊ ትግሉንም በአሁኑ ወቅት እየገፋ ይገኛል። በዚህ ወቅትም የረፈረንደም ቀን ይቆረጥልኛል በሚል ጽኑ እምነት የተለያዩ መድረኮችንና ሰላማዓዊ ሰልፎችን በማድረግ ቀኑ መዝገየቱን አሳውቋል።

ይሁን እንጂ ይኼ ታሪካዊ ጥያቄን በህገ-መንግስታዊ መንገድ ይመለሳል ብሎ ሲጠባበቅ ለቆየው ብሔርም ሆነ ትግሉን በፊለፊት እየመሩ ላሉት ኤጄቶዎች በማያገባቸው እየገቡ ከዚህ ቀደም ደም እንዳፈሰሱ እንደለመዱት ያንን ለመድገም የሚያሰሩ ፖለቲከኞች ስብስብ መደራጀቱንና ጥያቄውን ለማድብዘዝ አመራር በማሸማቀቅ ጥያቄውን ለመቀልበስ የሚከጅሉ እንዳሉ ደርሰንባቸዋል።

ደኢህዴን ጭምር ለዚህ ዋና ተዋናይ መሆኑን አምነን በቅርቡ የነበራቸው ስብሰባ እንዲበትኑ ሆኖአል። በቀጣይም ስብሰባውን አቃርጦ የወጡትን ጀግና አመራሮቻችንን በአጉል ስብከት ለማስማማትና ይቅርታ ጠይቁ በማለት በማስገደድ ላይ ይገኛል።

ደኢህዴን በኢህገ-መንግስታዊ አካሄድ እድሜውን ለማራዘም የሲዳማን ክልል የመሆን ያለቀ ጥያቄ ጋሬጣ እየሆነ ስለሆነ የረፈረንደም ቀን ተቆርጦ እስካልተነገረ ተከታታይ አቋሞችን ኤጄቶ ለመያዝ ይገደዳል።

የሽማግሌ ሾንጎም ኤጄቶን መርቆ የትግሉን ችቦ በማስረከቡ በሲዳማ ምድር ለ3 ቀናት የሚጸና የስራ ማቆም አድማ እናደርጋለን።

ቀኑ:- መጋቢት 4-6/2011 ዓ.ም ነው።

የማይሰሩ መስራያ ቤቶች
…በሀዋሳ ምድርና በሲዳማ ዞን ውስጥ ያለ የፈዴራል፣ የአሮገ ክልል፣ በከተሞችና በዞኑ ወረዳ እስከቀበሌ ያሉ የመንግስት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ባንኮች፣ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እስከ LKG፣ የግል ድርጅቶች ጨምሮ ለሶስቱም ቀን ካለምንም ማስጠንቀቂያ መዝጋት ይጠበቅባቸዋል።

በቀኑ የማይዘጉ አገልግሎቶች

የህክምና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ ፖሊስ መስሪያ ቤቶች ፣ ፍርድ ቤቶች፤ የንግድ ሱቆችና የምግብ መጠጥ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ ገበያዎች፣ የመንገድና ትራንስፖርት አገልግሎት፣ የኃይማኖት ተቋማት፣ በንሳ ኤፍ ኤም፣ የውሃ፣ የመብራትና የቴሌ አገልግሎቶች በተለመደው አኳሃን ሥራቸውን ለመስራት ይገዳሉ/በእነዚህ ቀናትም የተለመደ ሥራቸውን ያከናወናሉ።

ማስጠንቀቂያ!
# የደኢህዴን ቢሮችና ጽ/ቤቶች ከቅዳሜ ጀምሮ እንደተዘጉ ይቀጥላሉ።

ማንኛውም በደኢህዴናዊ ዓይን የተቃኘ ስብሰባ ለመሰብሰብ ይቅርና ያሰበ ጠሪም ሆነ ተጠሪ የተከለከለ ነው። የሲዳማን ክልል ጥያቄ ጉዳይን ለመወያየት እንደ አጀንጃም ሆነ እንደመነጋገሪያ ተደርጎ የሚቀርብ ስብሰባ ላይ መገኘት የተከለከለ ነው። ከዚህ ውጪ እንቀሳቀሳለሁ የሚል የሲዳማም ሆነ ሌላ ተለጣፊ አመራር ካለ ካለምንም ቅድሜ ማስጠንቀቂያ ኤጄቶ እርምጃ ይወስዳል።

በሶስቱ ቀናት ውስጥ በተዘጉ መ/ቤቶች ቢሮ ገብቶ ሲሰራ የተገኘ አካል ወይም ቡድን ላይ ኤጄቶ ባለው አደረጃጀት ተመጣጣኝ እርምጃ ይወስዳል።

በእነዚህ ቀናት ውስጥ የማንኛውም ግለሰብ ንብረት ኤጄቶዎች ከያዙት አቋም ውጪ ሆኖ ሲሰርቅ፣ ሲዘርፍ፣ ከግለሰቦች ጋር ለጥልና ለስድብ ለሚነሳ፣ የሰውን አካል በማጉደል የሚሳተፍ ማንኛውም ግለሰብና ቡድን ላይ እርምጃ ይወሰዳል። አስፈላጊ ሆኖ ስገኝም ለህግ-ተላልፎ ይሰጣል።

ባለሀብት ነን በማለት ሰርቀው በልጽገው የሚኩራሩትንና ሲዳማን የሚጎዳ ደኢህደናዊ ስራ የሚደግፉ አካላት ላይ ጠንካራ እርምጃ ይወሰዳል። የሚኩራሩትን ሀብታቸውን ከጥቅም ውጪ እስከማድረግ።

ስልጣን በመመካት የሚንቀሳቀስ ማንኛውም ፖለቲከኛ ሆነ አደረጃጀት ላይ መረጃ ጎን ለጎን በመላክ እርምጃ ይወሰዳል።

የረፈረንደሙ ቀን ባለነው ሳምንት ቀኑ ተቆርጦ ለህዝባችን ካልተገለጸ ድረስ ቀጣይ ተከታታይ እገዳና የባሰ ማዕቀብ ለማወጅ ጨርሰን እየተጠባበቅን እንገኛለን። ኤጄቶም በየቦታው በተጠንቀቅ ይንቀሳቀሳል!

ታግለን መብታችንን የሚናስከብር እንጂ በችሮታና በድርጅቶች መልካም ፈቃድ የሚሰጥ መልስ ተቀባይነት የለውም!

“ይህ ለሲዳማ ህዝብ አርነት የሚታገል የመጨረሻው ህዝብ ነው!”

እውነት ትፍረድ!

ኤጄቶ
ሀዋሳ

ሲዳማ

ኢትዮጵያ

በመላው ዓለም የሚኖሩ የሲዳማ ተወላጅ ኢትዮጵያዉያን በወቅታዊ የሲዳማ ጉዳይ ላይ ያወጡት የአቋም መግለጫ

በመላው ዓለም የሚኖሩ የሲዳማ ተወላጅ ኢትዮጵያዉያን በወቅታዊ የሲዳማ ጉዳይ ላይ ለመምከር በማርች 10 ቀን 2019 አስቸኳይ ስብሰባ አድርገዉ የሚከተለዉን ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ አዉጥተዋል።

1ኛ. የሲዳማ ሕዝብ ላለፉት በርካታ አመታት የራስን እድል በራስ ለመወሰንና የራሱ የሆነ ክልላዊ መዋቅር ዘርግቶ ለመተደደር የአገርቱን ህገመንግስት ተከትሎ ፍጹም ሠላማዊ በሆነ መንገድ የጠየቀውንና የተለያዩ ደረጃወችን አልፎ ህዝቤ ውሳኔ እንድያደራጅ ለምርጫ ቦርድ የቀረበውን ጥያቄ ለማስተጓጎል ደኢህዴን የሚያደረገውን ማንኛውንም ህገ ወጥ ዘመቻ አጥብቀን እንቃወማለን።

2ኛ. የሲዳማን ሕዝብ ሲዳማ ለማድረግና በሲዳማ እንድሁም በአከባቢው ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግር ለመቅረፍ፥ በሕዝቦች ፍለጎት ላይ የተመሰረተች፣ ፈደራላዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት የተዘርጋባት፣ የዜጎች እኩልነትና ፍትህ የሰፈነባት እና ሕዝብ የሥልጣን ባለቤት የሆነባትን ኢትዮጵያ ለመገንባት የሚታገለውን የሲዳማ ባለራዕይ ትውልድ የኤጄቶን ሠላማዊ ትግል በመሉ ልብ እንደግፋለን።

3ኛ. በሲዳማ የለውጥ ኃይል እና የመልካም አስተዳደር ናፋቂ ትውል ኤጄቶ ላይ የሚደረግ ስም የማጥፋትና የማጥላላት ዘመቻን አጥብቀን እንቃወማለን።

4ኛ. ሲዳማንና የሀዋሳን ከተማ ለማለያየት የሚደረግ ማንኛውንም እንቅስቃሴ እንድሁም ለየብቻ የሚደርግ የሕዝብና ቤት ቆጠራ በሲዳማ ህዝብ ሉአላዊነት ላይ የሚደረግ ጦርነት በመሆኑ አጥብቀን እንቃወማለን።

5ኛ. ደኢህዴን በሲዳማ ሕዝብ ጉዳይ ላይ የምያሳልፈውን ማንኛውንም ኢህገመንግሥታዊና እራሱ ደኢህዴን በምክር ቤቱ የወሰነውን ውሳኔ በመሻር የሲዳማ ሕዝብ ክብር የሚነካና መርዎቹን የምያሸማቅቅ እንዲሁም የለውጥ ሀዋርያ ኤጄቶን የሚያጥላላ በተጨማሪም የሲዳማ ሕዝብ ከሊህቅ እስከ ደቅቅ ከልጅ እስከ አዋቂ በጋራ የጠየቀውን ህገመንግሥታዊ ጥያቄ የሚያንቋሽሽ ሰነድ አጥብቀን እንቃወማለን።

6ኛ. በሲዳማ ተወላጅ የደኢህዴን ተላላኪወችና የፈዴራል ስርዓት ተቃዋሚ ኃይሎች ቅንጅት በሲዳማና በአከባቢው በሚኖሩ ሕዝቦች መካከል ልዩነት ለመፍጠር እንዲሁም የሲዳማን ሕዝብ ለመከፋፈልና ለማለያየት የምደረገውን ማንኛውንም አይነት ሴራ አጥብቀን እንቃወማለን።

7ኛ. በማንኛውም ጊዜ በሚቻለን ሁሉ በሲዳማ ሕዝብ መርዎችና በኤጄቶ ጎን ለመቆም ያለንን ዝግጁነት በአጽንዖት እንገልፃለን።

8ኛ. የሲዳማ ሕዝብ ከደኢህዴን የሚደረግበትን ትንኮሳ ሳይበገር ሠላማዊና ህገመንግሥታዊ ጥያቄውን ከዳር ለማድረስ ከመቼውም በላይ አንድነቱን ጠብቆ በመመካከርና በመደማመጥ እንድጓዝ በአጽንዖት እንጠይቃለን ።

9ኛ. የኢትዮጵያ መንግስት እና ምርጫ ቦርድ ለሲዳማ ሕዝብ ህገ መንግሥታዊ ጥያቄ በህገመንግሥት ላይ ብቻ የተመሰረተ ውሳኔ ለመስጠት በአስቸኳይ ህዝቤ ውሳኔ እንዲያደራጅ አጥብቀን እንጠይቃለን ።

10ኛ. በሀገርቷ ላይ የመጣዉን ለዉጥ ሙሉ በሙሉ የምንደግፍ መሆኑንና ይህንን ደግሞ ወደኃላ ለመቀልበስ የሚደረገዉን ማንኛዉንም ዓይነት እንቅስቃሴ አጥብቀን የምንቃወም መሆኑን እንገልጻለን።

“ዳግም በሲዳማ ምድር ፀሀይ አትጠልቅም” እግዚአብሄር አገራችንን ኢትዮጵያ ይባርክ አሜን!!
የሲዳማ ዲያስፖራ ማህበረሰብ
ማርች 10 ቀን 2019
ከመላው ዓለም!